Berry - Helina Lyrics

Lyrics Helina - Berry



ማን ቀድሞ አይቶ
መልኩን አውቆ በልጦ
መርጦ መጣ
ጠቁሮ አይነጣ
ሁሉ አብሮት እንጂ
ሰው ተማክሮ
መች ራሱን ፈጥሮ
እንዲህ አብሮት እንጂ
ህሊና ይህን ካላስተዋለ
ሰውን በዘር ኮናኝ ብዙ አለ
ህሊናን ጥሎ ካታለለ
የጠቢብ ዘር ነኝ ባይ ከንቱ አለ
ማን ቀድሞ በልጦ
ዘር ነገድን መርጦ
መች ተወለደ
አውቆ ፈቀደ
ምን ያርግ እንግዲ
እርሱን ዳኛ እንዲ
ሁሉ አብሮት እንጂ
ህሊና ይህን ካላስተዋለ
በላጭ ኩሩ ነኝ ባይ ብዙ አለ
ህሊናን ጥሎ እያታለለ
ሰውን በዘር ኮናኝ ከንቱ አለ
ህሊና ይህን ካላስተዋለ
በላጭ ኩሩ ነኝ ባይ ብዙ አለ
ህሊናን ጥሎ እያታለለ
ሰውን በዘር ኮናኝ ከንቱ አለ
ህሊናን ጥሎ እያታለለ
በላጭ ኩሩ ነኝ ባይ ብዙ አለ




Berry - Kemin Netsa Liwita
Album Kemin Netsa Liwita
date of release
08-12-2015




Attention! Feel free to leave feedback.