Gigi - Hulu-Dane Lyrics

Lyrics Hulu-Dane - Gigi



️ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሀሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሁኜ
አንተን አሞኜ ምን ሁኜ
ቅዱስ ሀያል እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን
ከጨለማው አውጥቶ ወደ ብርሃን የመራን
ከሰማይዋዊው ሰማይ በክብር ይመጣል ጌታ
በመላእክት ታጅቦ በሙዚቃ በእልልታ
አንተን ያመነ ሀሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሁኜ
አንተን አሞኜ ምን ሁኜ
እናታለም ደግሽ የልጅሽ ሰርግ ደረሰ
ሞትን ሲኦልን በጣጥሶ እየሱስ ክርስቶስ ነገስ
ኤደን ገነት እልል በይ እናታለም እልል በይ
አባታችን ቤት ሰራልን ከመንግስታት ሰማይ
አንተን ያመነ ሀሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሁኜ
አንተን አሞኜ ምን ሁኜ
በጨለማ በድቅድቅ በሲኦል የተዘጉትን
እየነዳ አወጣቸው ወደ ብርሀን ልጆቹን
ይወደናል አምላካችን ይቅር ባይ ነው የኛ ጌታ
ምህረት ፍቅሩ ለዘለዓለም ክንዱ ለእውነት የበረታ
ሁሉን አጋዥ ሁሉን ጧሪ የሁሉ አባት መካሪ
ባልሽ ምትክ የለውም ፅዬን ብርሀንሽን አብሪ
በእንቁ በአልማዝ ተሸለሚ ቅድስት እየሩሳሌም
እናታችን ደስታችን ለዘለዓለም አለም
አንተን ያመነ ሀሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሁኜ
አንተን አሞኜ ምን ሁኜ



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Gigi - Gold & Wax
Album Gold & Wax
date of release
16-05-2006




Attention! Feel free to leave feedback.