Gossaye Tesfaye - Betesasate Silk Lyrics

Lyrics Betesasate Silk - Gossaye Tesfaye



በተሳሳተ ስልክ በድንገት ድምጿን ሰምቼ
ሳወራ ብቆይ ከሷ ጋር ጉዳዬን ትቼ
እጇን የመራው ወደ ስልኬ
ሊያገናኘን ነው ለካ እሱ አምላኬ
አሁን ብናገረው እስኪ እንደው እኔን ማን ያምነኛል (ያምነኛል)
ሳስበው ደግሞ ለራሴም ግርም ይለኛል
የባጥ የቆጡን ዘላብጄ
የኔ አደረኳት በቃ ገባች ከእጄ
አወይ አጋጣሚ ምክንያት አርጎ የስለኩን ጥሪ
(ገና ገና-ገና)
ድምጻን ገና ስሰማው ገና
ልቤ አረፈው ወደዳትና
(በጣም ኦው በጣም)
በፊት ያኔ ይህ ሳይሆን ገና
እሷን መሳይ መች አሰብኩና
(ገና ገና-ገና)
ለሷም ለኔ ፍቅር የገመደው
ለካ ቀድሞ አምላክ አዞት ነው
በቃ ደስ አለኝ ልቤ አልፎ ነጋልኝ ዛሬ
ሲደርስ ሀሳቤ
ሲደርስ... ሲደርስ ሃሳቤ
ሲደርስ ሃሳቤ
ሲደርስ... ሲደርስ ሃሳቤ
የእጇ ስህተት ቁጥሩን ደባልቆ
ካልታሰበው ከስልኬ ዘልቆ
(ገና ገና-ገና)
በቀጭኑ ድምጽ አዛይ ሽቦ
ገባ ፍቅሯ ልቤን ተብትቦ
(ገባ ገባ-ገባ)
ስፈልገው ስመኘው ኖሬ
የሷን እሩብ እኔ እስከዛሬ
(ገና ገና-ገና)
አምላክ ደጉ ጣቱን ሰጣት
ደውይ አላት አዲሱ ቤቷ
ቀልቧ ከቀልቤ ተናቦ
ገባ በቀጭኑ ሽቦ ፍቅሯ እኔን ስቦ
ስቦ
በቀጭን ሽቦ
ስቦ
አስቀረኝ ስቦ
ድንገት
ጮኧና ስልኬ
ሳሳሁ
(ኧረ እኔ ሳሳሁ)
ሳሳሁ
(ኧረ እኔ ሳሳሁ)
እንኳን
ስልኳን አነሳው



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Album Siyamish Yamegnal
date of release
06-01-2019




Attention! Feel free to leave feedback.