Sami Dan - Hager Malet Lyrics

Lyrics Hager Malet - Sami Dan



ከሞቀው ጎጆ ከሚስት ልጁ ተነጥሎ
ያፈራውን ሁሉ ቀዬ መንደሩን ሁሉን ጥሎ
ከመሰሎቹ ስንቁን ሸክፎ ቶሎ በል እያለ
የልቡ ላይ እሳት ስሜቱን ቢያንረው እየገነፈለ
ተነሳ እያለ እየተመመ
ተደፈርኩኝ ብሎ በቁጭት ታመመ
ባሳቡ ለሳላት በሆዱ ላዘላት
ሄዶ በቃ ሊሞትላት ከሀሩር ገባላት
ሀገር ማለት
ካሳብ የገዘፈች ትልቅ ምታስጠልል ዋርካ ጥላ
ሀገር ማለት
ስትኖር ምታኖር ስጠፋ ምንጠፋ ታላቅ ሚስጥር
ሀገር ማለት
የትም አለም ስንዞር በልባችንም ውስጥ የምንሸከማት
ሀገር ማለት
ከወዛችን ላይ አለች ከገፃችን አለች እኛ ላይ ተስላ
ከጦር ሜዳው ገብቶ ቢጎዳም ግድ የለው
የሷ ፍቅር እንጂ ልቡን ያገዘፈው
ክብሯማ ሲነካ በቁም ከማይ ብሎ
ይሞታል ጀግናዋ አደራ አቀብሎ
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ የተባለችው ሀገር
አንደኛ እናትህ ናት
ሁለተኛ ክብርህ ናት
ሶስተኛ ሚስትህ ናት
አራተኛም ልጅህ ናት
አምስተኛም መቃብርህ ናት
እንግዲህ የእናት ፍቅር የዘውድ ክብር የሚስት የዋህነት
የልጅ ደስታ የመቃብር ከባቢነት እንዲህ መሆኑን እወቅ
ካድማሱ ወዲያ ተሻግሮ ሄዶ ሰው ሀገር ላይ
ሀብት ስልጣኔ ልቡን የሚያሸፍት አይቷል ሲሳይ
የሰማይ የምድር እርቀቱን አይቶ እንዴት ሆነ እያለ
ማነው የጎተተኝ በሚለው ጥያቄ ተብሰለሰለ
ተነሳ እያለ እየተመመ
ተደፈርኩኝ ብሎ በቁጭት ታመመ
ባሳቡ ለሳላት በሆዱ ላዘላት
ሄዶ በቃ ሊሞትላት ከሀሩር ገባላት
ሀገር ማለት
በብዙ ሰው ሀሳብ ውስጥ ምትመላለስ ምታብሰለስል
ሀገር ማለት
ሲዳብሷት ምትሞቅ መአዛዋ ሚሸት ድንቅ ፍጥረት
ሀገር ማለት
ምድራዊ ፍጥረቷ ከዘመን ተሳስሮ ትዝታን የሚያጭር
ሀገር ማለት
ቢርቋት የምትቀርብ ሲቀርቧት ምታቅፍ እናት ነገር
መች ሊረሳት ደግሞ ትዝታው ናት ለሱ
ሲመጣ ሚለብሳት እንደ ብርድልብሱ
ሙቀቱም ናትና ለውስጥ ቁርጥማቱ
ወጌሻው ሀኪሙ ለልብ ስብራቱ
ኢትዮጵያ ሀገሬ መመኪያዬ ክብሬ
ኢትዮጵያ ሀገሬ ዞሮ መግቢያዬ በሬ
ኢትዮጵያ ሀገራችን መመኪያ ክብራችን
ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን
ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን



Writer(s): Sami Dan


Sami Dan - Sibet
Album Sibet
date of release
01-09-2021




Attention! Feel free to leave feedback.