Betty G - Ay Zendro paroles de chanson

paroles de chanson Ay Zendro - Betty G



የታል በበጎ በክፉ ጊዜ፥ ፍጹም ላንለያይ ቃል የገባነው ያኔ፥
ዘንድሮ ምን የተለየ ፥ነገር ተከሰተ፥ እንዲህ ልብ ያሸፈተ
"መጋጨት ያለ ነገር" ነው ትለኝ አልነበረ፥ በኛም አልተጀመረ፥
የኔ መስነፍ ያንተም መሰላቸት፥
እኛን አለያየን የሁለታችንንም ልብ ሰበረ፥
"ፍቅር ይታገሳል፥ ደሞም ቸርነት ያደርጋል፥ እንዲሁ አይወድቅም ከቶ"
(ፍቅር ፍቅር ፍቅር)
ስናበላሽ እንዲህ እያልክ፥ ትመልሰኝ አልነበር፥ ለምን ልብህ ዛለ ቶሎ፥
(ፍቅር ፍቅር ፍቅር)
አይ ዘንድሮ ጥሬ ዞሮ፥
አልበሰልንም፥ አዋቂ እኛን ብሎ፥
ፍቅር አይታበይም፥ በደልንም አይቆጥርም፥ በመለያየት አያምንም፥
ፍቅር ይታገሳል፥ ደሞም ቸርነት ያደርጋል፥ አይወድቅም ከቶ፥
(ፍቅር ፍቅር ፍቅር)
ፍቅር ተስፋ ያደርጋል፥ ፀንቶም ይቆማል፥
(ፍቅር ፍቅር ፍቅር)
አይ ዘንድሮ (አይ ዘንድሮ) ጥሬ ዞሮ (ጥሬ ዞሮ)፥
አልበሰልንም፥ (አዋቂ) አዋቂ እኛን ብሎ፥



Writer(s): Yamlu Mola


Betty G - Wegegta
Album Wegegta
date de sortie
21-06-2018




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.