Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gud Fella paroles de chanson

paroles de chanson Gud Fella - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



የተውኩትን ነገር ተመክሬ ተነግሬ በሀገር
ምን ጎትቶ አመጣብኝ ያኔ ያረጀ ያን የድሮ ፍቅር
ጉድ ፈላ ዘንድሮ አቤት አቤት ማን አስተማረብኝ
ማስቲካ ሆኛለሁ ከረሜላ ከአፉ አሳደረኝ
ይኽው ይሰማኛል ጡሩንባ
ይኸው ይነፋሉ ጡሩንባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ሀፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ
እዩት ልጁን፤ ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን፤ ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ፤ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት፤ በዚህ ጉዳይ
ውብ ቁመና፤ ወየው ዛላ
ሰው እንደ እህል፤ አይበላ
አለ ለካ፤ የሰው ሀረግ
ደረት ክንዱ፤
ባለ ማዕረግ ባለ ማዕረግ
እስቲ በጆሮዬ ፍቅርን ይድገም ያነብንብልኝ
ከትንፋሹ በልጦ የሚደመጥ ምን ሙዚቃ አለኝ
በእጁ ቢነካካኝ ድምፅ አወጣው እኔም እንደ ጊታር
ጉድ አረገኝ መውደድ ጉድ አረገኝ የዚህ ሰው ፍቅር
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ልቤን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ አርገኝ የቤትህ እመቤት
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ሀፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ፤ ልቤ ለፍቅርህ እያደላ
ስንት አጥምደህ፤ ስንት ይዘሀል
ስንቷን ቆንጆ፤ አፍዝዘሀል
የሴት ሁሉ፤ ቃል ማረፊያ
ክንፍ አለህ ወይ፤ ማንሳፈፊያ
እንዴት ብዬ፣ ላወዳድርህ፤ ከዚህ ሁሉ፣ ኮሳሳ
ቢጠይቁኝ፣ ልንገራቸው፤ ጀግንነትክን፣ የኔ አንበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
(ጉድ ነው ጉድ ነው)
ይኽው ይሰማኛል ጡሩንባ
ይኸው ይነፋሉ ጡሩንባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ሀፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ
ስንት አጥምደህ፤ ስንት ይዘሀል
ስንቷን ቆንጆ፤ አፍዝዘሀል
የሴት ሁሉ፤ ቃል ማረፊያ
ክንፍ አለህ ወይ፤ ማንሳፈፊያ
እንዴት ብዬ፣ ላወዳድርህ፤ ከዚህ ሁሉ፣ ኮሳሳ
ቢጠይቁኝ፣ ልንገራቸው፤ ጀግንነትክን፣ የኔ አንበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ የኔ አነበሳ
(ጉድ ነው)
የኔ አንበሳ የኔ አንበሳ
ጉድ ነው ጉድ
ይኽው ይሰማኛል ጡሩንባ
ይኸው ይነፋሉ ጡሩንባ
እልልታው ጭፈራው ደመቀ
ፍቅሬ ተመልሶ ገባ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ኧረ ጉድ ኧረ ጉድ ፈላ
ሀፍረት ይሉኝታዬን አሳጣኝ
ልቤ ለፍቅርህ እያደላ
እዩት ልጁን፤ ሲንጎራደድ
ያንን ሽንጡን፤ ሲያውረገርግ
አይኑ ገዳይ፤ ጥርሱ ገዳይ
ስንቴ ልሙት፤ በዚህ ጉዳይ
ውብ ቁመና፤ ወየው ዛላ
ሰው እንደ እህል፤ አይበላ
አለ ለካ የሠው፤ ሀረግ
ደረት ክንዱ
ባለ ማዕረግ ባለ ማዕረግ
አቤት አቤት አቤት አቤት
አቤት አቤት አቤት አቤት
ፍቅሬን ላንተ ሰጥቻለሁ አርገኝ የቤትህ እመቤት



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gigi
Album Gigi




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.