Teddy Afro - Emma Zend Yider (Live) paroles de chanson

paroles de chanson Emma Zend Yider (Live) - Teddy Afro



እማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ፡፡
ዘብ ኖሮ ለኔ ገላ
ደግሞ አያለሁ ካንቺ ሌላ
ልምጣ ወይ ልቅር ምን ይሻለኛል
ከፍቅርሽ 'ሚያስጥል
ማን ዘንድ ይገኛል፡፡
ስለት አለብኝ ከርቤ እና እጣን
ለመተያየት እንዲያበቃን፡፡
የጠቢቡ ሰው የሊቁን ቅኔ
ህልሜ አይፈታም ሳላይሽ ባይኔ፡፡
እማ ዘንድ ይደር ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ካላንቺ እኔ፡፡
ማዘብ ኖሮ ለኔ ገላ
ደግሞ አያለሁ ካንቺ ሌላ፡፡
የብራና ስዕል አይነ ጎላዬ
መልከ ማክዳ ሳባ መሳዬ፡፡
የሸማሽ ጥለት ቀልሞ ሰንደቄ
ያስታውሰኛል ላንቺ መውደቄ፡፡
ልቤ አምሮህ ሌላ ዝቅ አትበል ይቅር
ሃገር ያህላል ከፍ ያለ ፍቅር፡፡
ዘንግ ይዞ ገብቶ ገዳም
ያገናኘው ፍቅርን ካዳም፡፡
ፆም ይዞ ቆጥሮ ጠጠር
ባሳከለው ፍቅርን ሃገር...
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር ×2
ሰው አሳዝኖ ሰው ላይሆን ነገር
ምን አስጀመረዉ የማይሆን ነገር፡፡
ልቤ አንቺን ትቶ ከማን ዘንድ ይደር
ልማልልሽ ወይ 'ቶ' መስቀሌ
ከራሴ ጋር ነው ብጣላሽ ጥሌ፡፡
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር...
ድር ተርታሪ ጥልፍ የጠለፈው
አስዋብኩሽ ብሎ ምን አስጎበረው ፡፡
ሸማ ተጊጦ ቀለም ቢነከር
ልብስ አያምርበት ያ'ራቁት ሃገር፡፡
ልምጣ ወይ ልቅር አጣሁ መንገድ
እግሬ እንዴት ይጥፋው
ቆርጦ መሄድ፡፡
እይ ሰው ሲወጣ እይ ሰው ሲወርድ
እንዲህ አይደለም ወይ መራመድ
ይህ አይደለም ወይ መራመድ
ዘንድ ይደር ዘንድ ይደር
እማ ዘንድ ይደር...



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Ethiopia Wede Fikir (Live)
Album Ethiopia Wede Fikir (Live)
date de sortie
29-04-2019




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.