Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Hulu-Dane текст песни

Текст песни Hulu-Dane - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን አምኜ ምን ሆኜ
ቅዱስ ሀያል እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን
ከጨለማው አውጥቶ ወደ ብርሀን የመራን
ሰማያዊው ሰማይ በክብር ይመጣል ጌታ
በመላዕክት ታጅቦ በሙዚቃ በእልልታ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን አምኜ ምን ሆኜ
እናት አለም ደግሺ የልጅሽ ሠርግ ደረሰ
ሞተን ሲዖልን በጣጥሶ እየሱስ ክርስቶስ ነገሰ
ኤደን ገነት እልል በይ እናት አለም እልል በይ
አባታችን ቤት ሰራልን ከመንግስታት ሰማይ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን አምኜ ምን ሆኜ
በጨለማ በድቅድቅ በሲኦል የተዘጉትን
እየነዳ አወጣቸው ወደ ብርሀን ልጆቹን
ይወደናል አምላካችን ይቅር ባይ ነው የእኛ ጌታ
ምህረት ፍቅሩ ለዘላለም ክንዱ ለእውነት የበረታ
ሁሉን አጋዥ ሁሉን ጧሪ የሁሉ አባት መካሪ
ባልሽ ምትክ የለውም ፂዮን ብርሀንሽን አብሪ
በዕንቁ በአልማዝ ተሸለሚ ቅድስት እየሩሳሌም
እናታችን ደስታችን ለዘለዓለም አለም
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
አንተን ያመነ ሁሉ ዳነ
እኔ አንተን አምኜ ምን ሆኜ
አንተን አምኜ ምን ሆኜ



Авторы: Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gold & Wax
Альбом Gold & Wax




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.