Gigi - Sew Argen текст песни

Текст песни Sew Argen - Gigi



ዓይኑ ማረከኝ ስል ከንፈሩ ገሎኛል
ደሞ ከሞትኩበት ፍቅር ያስነሳኛል
Dear my love ይለኛል ከዚያም የኔ ፍቅር
ስንቱን ቋቋ ችዬ ከሱ ልነጋገር
ጉራማይሌ ልጅ ጉራማይሌ ቋንቋው
ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
ጉራማይሌ ልጅ ጉራማይሌ ቋንቋው
ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
የተቀባው ሽቶ የገላው ጠረነ
ብሉኝ ብሉኝ ይላል የቀረቡት እንደሆነ
ከከፈር ከጥርሱ ከአይኑ ፍቅር ይዞኝ
እወዘወዛለሁ እረ ማን ያስጠለኝ
አካል ሰውነቱ እንደ ህፃን ልጅ
አቤት መለስለሱ አቤት ሲያስጎመጅ
የኔ እግር እንዳንተ ምን አለሰለሰው
ከኔ ቤት አንተ ቤተ የተመላለሰው
ጉራማይሌ ልጅ ጉራማይሌ ቋንቋው(2)
ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ(2)
እመቤቴ ማርያም አርጊልኝ የግሌ
በፈረንሳዮቹ ቋንቋ በእንግልዝኛ ቢናገር
በጣልያንኛ ቢገጥም በጀርመንኛ ቢፎክር
ከአፉ ማር ይፈሳል ልጅ ለዛ አለው አንደበቱ
እስቲ ይጫወት ይፈንድቅ ያለሱ አይደምቅም ቤቱ
ጨዋታህ ይናፍቀኛል ያራዳ ልጅ ቆንጆ ሰው
በለሰለሱ እጆችህ ገላዬን ደባብሰው
ጉራማይሌ
ጉራማይሌ፣
ጉራማይሌ



Авторы: Shibabaw Ejigayehu


Gigi - Gigi
Альбом Gigi
дата релиза
28-04-2003




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.