Gossaye Tesfaye - Selam Yisten текст песни

Текст песни Selam Yisten - Gossaye Tesfaye



ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
እንዲያው አንዳንዴ ይገርማል
ኧረ እንደው አንዳንዴስ ይደንቃል
እንዴት ተንዶ ፍቅራችን
ማነው ያራራቀን ከእውነት ቃል
በጊዜ አስታከን በዘመን
ራስ መውደድን አስቀድመን
ይቅርታ ራቀ ካፋችን
ዝና እየተቀማ ልባችን
አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን
የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን (እግዚኦ)
ማረን ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
ከዚ ፈተና
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
እግዚኦ መሐረነ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
ሰላም ይስጠን እግዜር ገናና
ከጋረደን ጥቁር ደመና
ጊዜው ይሆን እላለው እኔ
የሚሆነውን ሳስተውል በዓይኔ
በሀሜት በወሬ ታጅበን
በግላዊ ምቾት ተከበን
በዚች ጊዜያዊ ከንቱ ዓለም
ዘላለም ቋሚ ግን አንድ የለም
ንብረት ከሰው ልጅ አብልጠን
ክፋት ምቀኝነትን መርጠን
ዘመን አለፈ ስንኖር
የፅድቁን መንገድ የሚያሳይ አጥተን
አንቃን
ይብቃችሁ በለን የፍቅር አምላክ ጌታ
አንቃን
ቅድስቷን ምድር ሰላም አውርሳት ደስታ
አንቃን
ከቁጣ አብርደህ ቅን ወዳጅ አርገህ አንቃን
አንቃን
የት ይደረሳል ምን ይወረሳል ይብቃን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን (እግዚኦ አንጽአነ)
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን (እግዚኦ)
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ
እንዳንሆን አውጣን
ከዚ ፈተና (እግዚኦ)
አፋ ቅዱስ ሰው
ምግባሩ ሌላ (ምግባሩ ሌላ)
እንዳንሆን አውጣን
እግዚኦ መሐረነ
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፋ አድነን
አቤቱ አቤቱ
አውጣን ከመዓቱ
ማረን ማረን
ከክፉ አድነን



Авторы: Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Альбом Siyamish Yamegnal
дата релиза
06-01-2019




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.