Laeke - Reqiq Songtexte

Songtexte Reqiq - Laeke




አዎ እኔ ደርሶኛል የአስማቱ ጥሪ
ከባዕድ ምድር ያመራኝ ወደዚ
የማይታለፍ አጥር ያሳለፈኝ ቁልፉ
ደርሶ ከብቸኝነት ያነፃኝ እቅፉ
ድልም አልነበረ ከእርሱ
ልፋት ብቻ እኮ ነበር
ሕልምም አልሠለጠነ በዓለም
በቅዠት መንደር
ረቂቅ አትጠብቀኝ
አትፈልገኝ ከእርሱ
ከባዕድ ምድር ዉሰደኝ
ከባቢሎን ዉርሱ
አዎ እኔ ደርሶኛል የአስማቱ ጥሪ
ከባዕድ ምድር ያመራኝ ወደዚ
ረቂቅ አትጠብቀኝ
አትፈልገኝ ከእርሱ
ከባዕድ ምድር ዉሰደኝ
ከባቢሎን ዉርሱ



Autor(en): Fikru Semma



Attention! Feel free to leave feedback.