Sami Dan - Hagerigna Songtexte

Songtexte Hagerigna - Sami Dan




የዚህ ዘመን ሰው ነኝ
እዚች ምድር ምኖር ከሰው ዘር መገኛ
ሆኜ ነፀብራቋ
ማንነቴ ሁሉ ሀገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
አለም ተከፋፍላ ሁሉም በያገሩ
ከነባህላቸው ባሉበት ሲኖሩ
እኔም አንዱ ሆኜ ከነማንነቴ
የሌላን ሳልነካ ኖርኩኝ እንደ ቤቴ
ከነነፃነቴ
ባህሌ ውበቴ
ስጨፍር ስዝናና ሁሉም ባገርኛ
ስጣላም ስታረቅ ሁሉም ባገርኛ
ሰላምታዬም አክብሮቴም ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
የሀገሬ ሰው በቅኝ ያልተገዛ
አለው ብዙ ታሪክ ከአፈሩ የበዛ
ተጣልተው ማይችሉት በፍቅር የሚያስሩት
ከነሱ አንዱ ነኝ ሀበሽ የተባልኩት
ቀርበው የማይርቁት
ሁልጊዜም የሚያምኑት
ጋብቻዬም አይ ለቅሶዬም ሁሉም ባገርኛ
የማጌጠው የምለብሰው ሁሉም ባገርኛ
ፉከራዬም ሽለላዬም ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
(Oromiffa)
ፊደሉም የኔው ነው ቋንቋውም የራሴ
ከኔ ጋራ አድጓል ተጣብቆ ከነፍሴ
ማሙሽና ሚሚ አለ ሚጫወቱት
ከእናት ከአባታቸው ከአያት የወረሱት
ሁሌም የማይረሱት
አድገው ሚናፍቁት
ኩኩሉ አባሮሽ ሁሉም ባገርኛ
እቴ ሜቴ በዛ በበጋ ሁሉም ባገርኛ
ሆያሆዬ አበባይሆሽ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ



Autor(en): Getaneh Bitew


Sami Dan - Asira Andu Getsoche
Album Asira Andu Getsoche
Veröffentlichungsdatum
25-04-2019




Attention! Feel free to leave feedback.