Mahmoud Ahmed - Ambassel Lyrics

Lyrics Ambassel - Mahmoud Ahmed



አምባሰል ዳመና የ'ጅ ዝናብ ነው
አምባሰል ዳመና የ'ጅ ዝናብ ነው
መጣ ትዝታዋ የሚጋረደዉ
የባቲን ባሻገር ይሉታል አምባሰል
የባቲን ባሻገር ይሉታል አምባሰል
እህል እየበሉ ሰው ወዶ መሰልሰል
ደብር ላይ ሲደርሱ ይታያል የዝማ
ደብር ላይ ሲደርሱ ይታያል የዝማ
ከንፈርም ስንቅ ነው ላወቀበትማ
ያንባሰል ተሟጋች አያውቅም ይግባኝ
ያንባሰል ተሟጋች አያውቅም ይግባኝ
በበሽታዬ ላይ አንቺን ጣለብኝ
የንባሰል ዝንጀሮ ሲሄድ አጎንብሶ
የንባሰል ዝንጀሮ ሲሄድ አጎንብሶ
ሲመለስ ቀና አለ የልቡን አድርሶ
እንደምነው አይንሽ ጥቁርና ነጩ
እንደምነው አይንሽ ጥቁርና ነጩ
እንደባለስልጣን ቆራጩ ፈላጩ
አንቺ ምን ታደርጊ እኔ አኮራሁሽ
አንቺ ምን ታደርጊ እኔ አኮራሁሽ
ካልጠፋ ፍርምባ ልቤን ሰጥቼሽ
ልቤማ ልባሙ ሄደ ገሰገሰ
ልቤማ ልባሙ ሄደ ገሰገሰ
አይኔ በስንፍናው ቀረ እያለቀሰ
ያንባሰልን ዳገት ዝንጀሮ አይወጣውም
ያንባሰልን ዳገት ዝንጀሮ አይወጣውም
ሰው ከተፋቀረ እንከን አያጣውም
ያንቺን አመጡና ለኔ ነገሩና
የኔ ወሰዱና ላንቺ ነገሩና
ተደላድለው ተኙ አለያዩንና
(Ambasel Sound Playing)



Writer(s): Ahmed Mahmoud


Mahmoud Ahmed - Éthiopiques, Vol. 6: Mahmoud Ahmed (1973)
Album Éthiopiques, Vol. 6: Mahmoud Ahmed (1973)
date of release
04-07-2004




Attention! Feel free to leave feedback.