The Christians feat. Betty Tezera - Yene Geta New (feat. Betty Tezera) Lyrics

Lyrics Yene Geta New (feat. Betty Tezera) - The Christians feat. Betty Tezera




ሞገስ የጠገበ ክብር የተረፈው
ምሥጋና አምልኮ ገንዘቡ የሆነው
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
ሰማይ ምድሩ የተገረመበት
ለውበቱ የተነገረለት
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
ክብሩ ሰማያትን የከደነ
ምሥጋናው በምድር የተነነ
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ጌታ የኃያላን ጌታ
የአለቆች ጌታ የመሪዎች ጌታ የብርቱዎች ጌታ (፪x)
እግዚአብሔር እግዚአብሔር
የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (፪x)
የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (፪x)
አዶናይ ፀባዖት ኤልካዶሽ የሆነው
ራሱን ተማምኖ አውቆ እኔ ነኝ ያለው
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
ሰማያትን በስንዝር የለካ
ዓለማትን በእጆቹ የያዘው
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
ከዋክብትን በሥም የሚጠራ
በቀን በሌት ሁሉን የሚያሰማራ
እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (፪x)
የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ጌታ የኃያላን ጌታ
የአለቆች ጌታ የመሪዎች ጌታ የብርቱዎች ጌታ (፪x)
እግዚአብሔር እግዚአብሔር
የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (፪x)
የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (፪x)




Attention! Feel free to leave feedback.