The Christians - Alresawm paroles de chanson

paroles de chanson Alresawm - The Christians



ትዝ ይለኛል
ማንም አልነበረ ከጎኔ
ትናንት በበረሃ
ትዝ ይለኛል
አንተ ነህ ሃይሌን ያደስክልኝ
ሆነህ የህይወት ውሃ
ትዝ ይለኛል
የዛሬውን አይተህ ልጅ ሳለሁ
ለክፉ እንዳልተውከኝ
ትዝ ይለኛል
አሁን አልረሳውም ጌታዬ
ክበር ያከበርከኝ
አልረሳዉም(4)
አልረሳዉም(4)
ያንዳንዱ ቅንነት ቀን እስከሚወጣ
ያንዳንዱ ትህትና ዘመን እስኪመጣ
ለካ ሲያስመስል ነው እንዲያ የነበረ
ሲያገኝ መስሎኝ ነበር ጸባይ የቀየረ
አድነኝ ባርያህን አድነኝ
አድነኝ እንዲ ካለው ነገር
ዘመኔ ይለቅ በቤትህ
ጌታዬ አንተን በማክበር
አድነኝ ልጅህን አድነኝ
አድነኝ እንዲ ካለው ነገር
ዘመኔ ይጠቅለልልኝ
ጌታዬ አንተን በማክበር
ከቅኖቹ ጋራ ቀና ትሆናለህ
ከጠማማ ጋራ አንተም እንደዚያው ነህ
የዋሁን ከአንበሳ ጉድጓድ ስታተርፈው
ጠማማውን ንጉስ በትል አስበላኸው
መነሻ ሁሉ ዘንግቶ በትእቢት ለተወጠረ
ቢያስተውል ይበጀው ነበር ያላንተ ማንስ ከበረ
የሰጠኸው ካንተ ጋራ ነው መንገዱ ላይ ትቆማለህ
ሚመካ ሚኮራበትን ከእጁ ላይ ትበትናለህ
ለከበረ ነገር ነበር የጠራኸው
በጥቂቱ ረክቶ ትእቢት ባይወጥረው
ካስብክለት ክብር ስንቱ ሰው ጎደለ
ቅንነቱን ጥሎ ባልዋልክበት ዋለ
አድነኝ እኔስ አድነኝ
አድነኝ እንዲ ካለው ነገር
ዘመኔ ይለቅ በቤትህ
ጌታዬ አንተን በማክበር
አድነኝ ልጅህን አድነኝ
አድነኝ እንዲ ካለው ነገር
ዘመኔ ይደምደምልኝ
ጌታዬ አንተን በማክበር




The Christians - Ethiopian Protestant Mezmur
Album Ethiopian Protestant Mezmur
date de sortie
03-09-2015




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.