Hamelmal Abate - Andande текст песни

Текст песни Andande - Hamelmal Abate




ባንዴ ባንዴ የማይወደድ ባንዴ የማይጠላ
አሰብ አሰብ እያረጉ ካልሆነ በመላ
ኧረ ኧረረረ ዋል አደር እያሉ ካላዩት በስተቀር
ኧረ ኧረረረ ላይ ላዩን ሰው መስሎ ስንት አለ የሚቀየር
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
ይሆነኛል ብለው አምነው ከቀረቡት ሰውነቱን አይተው
ዘንድሮ ብዙ ነው እንደ ተልባ ስፍር የሚንሸራተተው
ከሰው ተላምጄ አብሬ እየበላሁ ብስቅ ብጫወትም
ጥድፍ ጥድፍ ብዬ ላይ ላዩን ባየሁት በወረት አላብድም
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
ይለፈኝ ይለፈኝ ይለፈኝ ዘንድሮ
ልቤም ልብ ገዝቷል ካለፈው ተምሮ
ያማረውን ሁሉ ሰው መብላት ቢወድም
ምላስ ያልቀመሰው ከጉሮሮ አይወርድም
ጣል ጣል አድርጌ ቦታ ያልሰጠሁት
ስንቱ ነው ትልቅ ሰው ሆኖ ያገኘሁት
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
ባንዴ ባንዴ የማይወደድ ባንዴ የማይጠላ
አሰብ አሰብ እያረጉ ካልሆነ በመላ
ኧረ ኧረረረ ዋል አደር እያሉ ካላዩት በስተቀር
ኧረ ኧረረረ
ላይ ላዩን ሰው መስሎ ስንት አለ የሚቀየር
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
ተወዳጅ እንዳለ ቅን ልቦና ያለው ፍቅርን የተቀባ
አለ ደግሞ ክፉ የተከናነበ የተንኮልን ካባ
እየካቡ መናድ እየያዙ መልቀቅ እንዳይሆን ነገሩ
አንዳንዴም ደግ ነው ሳይቸኩሉ ማየት ነገርን ከስሩ
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
ለቀንም ቀን አለው ለጊዜም ጊዜ አለው
ወተትም ሲረጋ ነው ቅቤ የሆነው
አየተረጋጉ ካላዩት በስተቀር
ዛሬም ከዛሬ አልፎ ነገ አይሆንም ነበር
ይለፈኝ ይለፈኝ ይለፈኝ ዘንድሮ
ልቤም ልብ ገዝቷል ካለፈው ተምሮ
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት
አንዳንዴ ይሆናል ያሉት
አይሆንም እንደገመቱት
አንዳንዴም አይሆንም ያሉት
ይገርማል ሆኖ ሲያገኙት



Авторы: Hamelmal Abate



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.