Sami Dan - Tefa Yemileyen (Live) текст песни

Текст песни Tefa Yemileyen (Live) - Sami Dan




በመቀጠል ጠፋ የሚለየን የሚለውን ነው የምንጫወትላችሁ
አዬ ጊዜ ስንቱን አየን
እኔ እና አንቺን ጠፋ ሚለየን
አኩርፈሺኝ አኩርፌያለሁ
ግን ሳይሽ ደሞ ረሳዋለሁ
በቃ ከንግዲህ አጣኋት ስል ቆይቼ
ለስንቱ ገላጋይ የሌለውን አውርቼ
በጣም የራቅኩ መስሎኝ ከቤቴ ጠፍቼ
ናፍቆሽ ገና ጅምሩ ሲገርፈኝ
እያሮጠ ካንቺ ደጃፍ ሲመልሰኝ
ያስገባኛል ልብሽ ምንም ሳይል እያቀፈኝ
በልብሽ ብልቤ ያለው ፍቅር
ፅናቱም ስንት ዘመን ሚያሻግር
ሳናቀው ስንገኝ አጥፍተን
መለሰን ወደ ቤት ፍቅራችን
እኔ ካንቺ አንቺ ደሞ ከኔ ሌላ
ማን አለን እስኪ ሚሆነን ከለላ
ምን ቢሄድ ምን ቢመጣ አውቀዋለው
አንቺን፣ አንቺን
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው
ፍቅርን አይሁ በኛ ላይ
እያጀበን ሲያኖረን ሳይ
ስንት ያሉለት የኛ ነገር
መጨረሻው ሁሌም ሲያምር
እኔም ሮጬ አንቺም ወደኔ መጥተሻል
ሁለታችንም እርስበርስ ተርበናል
መቼ ያለፈውስ ትዝ ይለናል
ቃልም የለ ካንድብቴ ካንደበትሽ
በዛው ቀርተናል እያየሺኝ እያይሁሽ
አንድም ሆኗል ይቅርታዬና ይቅርታሽ
በልብሽ በልቤ ያለው ፍቅር
ፅናቱም ስንት ዘመን ሚያሻግር
ሳናቀው ስንግኝ አጥፍተን
መለስን ወደቤት ፍቅራችን
እኔ ካንቺ አንቺ ደሞ ከኔ ሌላ
ማን ኣለን እስቲ ሚሆነን ከለላ
ምን ቢሄድ ምን ቢመጣ አውቀዋለው
አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው
በፅናት ልጠብቅ ከንግዲህስ አወኩት
በፍቅርሽ ነው ለካ እስከዛሬ የዳንኩት
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ነው እኔማ ምወደው
አንቺን ነው አንቺን ብቻ ነው እኔማ ምወደው
እናመሰግናለን



Авторы: Samuel Alemu, Sami Dan



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.