Sami Dan - Kalsh Anchi Lyrics

Lyrics Kalsh Anchi - Sami Dan



ከፍቅር ፀበል ስንቴ አጠጣሽኝ
ከጥንካሬሽ ስንቴ አካፈልሽኝ
ተስፋ እንዳልቆርጥ ስንቴ አጠነከርሽኝ
ስበረታ አይዞህ አለሁ እያልሽኝ
እንዳልደክምብሽ ሁልጊዜ ትፈልጊያለሽ
ያለሽን ጊዜ በሙላ እኔላይ ታጠፊዋለሽ
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል
ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ጎኔ አለሽ አንቺ
ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሽ
አለሽ አንቺ አለሽ አንቺ ...
አይኔ ላይ ልቤ ላይ ቀልቤም ላይ አለሽ አንቺ
ሃሳቤም ላይ ቃሌም ላይ የማየውም ላይ አለሽ አንቺ
በደንብ እኔን ስላወቅሽኝ ነፃ ሰው አርገሽኛል
ለቤት ለፍቅራችን እንዴት አንደምሆን አስተምረሽኛል
እንዳልደክምብሽ ሁልጊዜ ትፈልጊያለሽ
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል
ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ጎኔ አለሽ አንቺ
ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሽ
ያለሽን ጊዜ በሙላ እኔላይ ታጠፊዋለሽ
ካለሽ አንቺ ለኔ ካለሽ አንቺ ሚከብደኝም ይቀላል
ያሰብኩትም ይቃናል
ግን ደግሞ አለሽ አንቺ ጎኔ አለሽ አንቺ
ብርታቴንም ጨምረሽ ድካሜንም አጥፍተሽ
ሳቄም ላይ ደስታዬም ላይ ስኬቴም ላይ አለሽ አንቺ
ጭንቀቴም ላይ ሐዘኔም ላይ እማባዬም ላይ አለሽ አንቺ
የእኔ ቆንጆ ባታውቀው ነው እንጂ አንተም ያው ነህ
ቃል ያጥረኛ አንተን የምጠራበት ምን ብዬ ልግለጽህ
ካንተ ጋር ነው ሁልጊዜም መኖር ነው የኔም ፍላጎቴ
ሐዘኔም ላይ ደስታዬም ላይ ሳቄም ላይ አለህ
ሰው በምድር ላይ ሲኖር አጋር ይሻል
ለእኔም አንቺን ሰጠ ልማዬን ሰምቷል



Writer(s): Sami Dan


Sami Dan - Keras Gar Negeger
Album Keras Gar Negeger
date of release
01-05-2016




Attention! Feel free to leave feedback.