Gigi - Kahn paroles de chanson

paroles de chanson Kahn - Gigi



በቃላት ድርድር በሙዚቃ ቃና
ስምን ስታብራራ ነፍስን ስታጣራ
አየሁኝ ጥበብ ሰማሁኝ ዕውቀት
ልናገር ልመስክር የዚህን ሰው እውነት
ቀልጦ እንደሚበራ ሻማ
መብራት በሌለው ከተማ
እየቀለጠ በራልኝ
እየሞተ አኑረኝ
የሱስ ባለእዳው ነኝ
ህይወት እንዳይሰለቸኝ
ሲጨነቅ ሰጠበብ
አይተኛም ቀን ከሌት
ለደስታዬ ሲዋትት
ካህንዬ የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
ካህን የነብሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
መሰንቆዉን ይዞ ከደጄ
ሲጫወት ያድራል ሲያዜም
በበገና በክራር ነፍሴን ሲያለመልም
እንደ መልከጼዴቅ ካህን
ክህነቱ ከዘመን ዘመን
የዘላለም አይደለም ወይ
የሰጠኝ ደስታ ከላይ
ስወድ ስጠላ የማይተወኝ
ለትንሽ ደስታው አመስጋኝ
አንዲህ ያለ ሰው የሰው ምርጥ
በጊዜ የማይለወጥ
ካህን የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
ቃል ካንደበቱ እንደውሃ
ይፈሳል እንደ ጅረት
ልብን የሚመረምር
ጠልቆ የሚገባ ከአንጀት
ሰምና ወርቁን ይናገር
ቅኔ መልሱን ይደርድር
በጻድቅ ሰው ቃላት
ነፍሴ ገባች ከገነት
ጣዕሙን ዜማ ስታዜም
ቃልን ከህይወት ስትቀምም
ስጋህን ለየህ ከነፍሴ
አቆራረጥከኝ ከእስትንፋሴ
ካህን የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
የነፍሴ አገልጋይ
እንቅልፍ አትተኛም ወይ
እንደ መልከጼዴቅ ካህን
ክህነቱ ከዘመን ዘመን
የዘላለም አይደለም ወይ
የሰጠኝ ደስታ ከላይ
ከላይ ከላይ
ከላይ ከሰማይ
ከላይ ከላይ
ከላይ ከሰማይ
አአአ... ከሰማይ



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Gigi - Gigi
Album Gigi
date de sortie
28-04-2003




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.