Gigi - Nafeken paroles de chanson

paroles de chanson Nafeken - Gigi



ኦወወወወ ናኣኣኣኣ ኦወወወወ ናኣኣኣኣ
ኦወወወወ ናፈቀኝ
ኦወወወወ ናኣኣኣኣ ናፈቀኝ
ናፈቀኝ የኛ ቤት ጨዋታ
ቁርስ ምሳ እራቱ የእምየ ፈገግታ
የዘመድ አዝማዱ ጨዋታ በካካታ
አንተየ'ይ
የጠላዉ ቤት ሌላ
የጠጁ ቤት ሌላ
ፋሲካዉ አያልፍም ሰዉ ጠግቦ ሳይበላ
የመጣዉ እንግዳ ሰክሮ ሳይጣላ
ናፈቀኝ ዛሬ በሰዉ ሃገር
ትዝታዉ ገደለኝ
የሰዉ ከብት እያየሁ እያንገበገበኝ
ዉሀ ጃሪዉ ወሀ ዉሀ ኮሎ ሲሉኝ
ያባቴም በሬዎች የእናቴም መሰለኝ
ሆ! ወሀ ጃሬ ወሀ ጃሬ
ወሀ ጃሬ ወሀ ጃሬ ይላሉ
ወሀ ጃሬ የናቴ በሬዎች ጥጆች
ወሀ ጃሬ ያባቴን ይመስላሉ
ወሀ ኮሎ ወሀ ኮሎ ወሃ ኮሎ
ወሀ ኮሎ ወሀ ኮሎ ይላሉ
ወሀ ኮሎ የእናቴ በሬወች ጥጆች
ወሀ ኮሎ ያባቴን ይመስላሉ
ስም የለኝም ስም የለኝ በቤቴ
ስም የለኝም ስም የለኝ በቤቴ
አንዱ እምየዋ ሲለኝ
አንዱ ሲለኝ አከላቴ
ጎኔ ሽኳሬዋ ሲሉኝ
በፍቅራቸዉ ሲጠሩኝ
ናፈቀኝ ጎረቤቱ
ናፈቀኝ ጨዋታዉ
ናፈቁኝ እህት ወንድሞቼ
አይጠፋም ትዝታዉ
ናፈቀኝ ደገኛዉ ቄስ ሞገስ
በፈረስ በበቅሎ ተጉዞ ሲመጣ
ለአመትበዓል ጨዋታ
ሰዉ እልል እያለ ሲቀበል በምቢልታ
አንተየ'ይ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
የሀገሩ ገነኛ እያለ ሲመጣ
አባየ ናፈቀኝ የከብቶቹ ጌታ
ሲባርክ ሲመርቅ የቤቱን ጨዋታ
እምየ እናት አለም
ጉልበትሽ ችሎታሽ
ይበልጣል ከሺህ ሰዉ
ያን ሰዉን ሁሉ እጅሽ ያጠገበዉ
ናፈቀኝ
ያያ ታዴ ሆዴ
የሽመል አቧራ አይችልም ገላየ
የኔ ሆድ አሌዋ ቁም ከኋላየ
አያና ደማሙ
አያና ደማሙ
አያና ደማሙ
አያና ደማሙ
አባይ ወዲያ ማዶ ትንሽ ግራር በቅላ
ልቤን ወሰደችዉ ከነስሩ ነቅላ
እየለ ሲዘፍን ትዝታዉ ገደለኝ
ዛሬ በሰዉ ሃገር
የሰዉ ከብት እያየሁ እያንገበገበኝ
ዉሀ ጃሬዉ ወሀ ወሀ ኮሉ ሲሉ
ያባቴም በሬዎች የናቴም መሰሉኝ .
ሆ! ወሀ ጃሬ ወሀ ጃሬ
ወሀ ጃሬ ወሀ ጃሬ ይላሉ
ወሀ ጃሬ የናቴ በሬዎች ጥጆች
ወሀ ጃሬ ያባቴን ይመስላሉ
ወሀ ኮሎ ወሀ ኮሎ ወሃ ኮሎ
ወሀ ኮሎ ወሀ ኮሎ ይላሉ
ወሀ ኮሎ የእናቴ በሬወች ጥጆች
ወሀ ኮሎ ያባቴን ይመስላሉ
ኦወወወዉ የቤቱ ጫወታ የመንደሩ ወሬ
ናፈቀኝ ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ
እህህ የየ ኦዉዎዎ ይይይ
ናፈቀኝ ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ
ኦዉ ዉዎዎ ዉዎዎዎ ዉዎ ይይይ
እእእ ይየ ይየየ ኦዉ ዉዎዎ እእእ ይይይይ



Writer(s): Shibabaw Ejigayehu


Gigi - Gigi
Album Gigi
date de sortie
28-04-2003




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.