Meskerem Getu - Lene Memotune paroles de chanson

paroles de chanson Lene Memotune - Meskerem Getu



ተስፋ ሰጥቶኝ ሄደ የርስቴን መያዣ
መንፈሱን ላከልኝ ለሕይወቴ ማደሻ
የዘለዓለም ሕይወት ማግኛ መንገዱን
አሳይቶኝ ሄዷል ለእኔ መሞቱን
አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (፬x)
በምድር እስካለሁ እስካሁን ድረስ
ሳዝን የሚያበረታኝ እምባዬን ሚያብስ
በርስቴ መያዣ በታሰብኩበት
ዘለዓለም እኖራለሁ በእርሱ መጽናናት
አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (፬x)
አሁን አውቄያለሁ የሚረባኝን
በኑሮዬ ሁሉ ላይ መሾም ያለብኝን
የእኔ መጀመሪያ ብሎም መጨረሺያዬ
ከምንም ከማንም በላይ ኢየሱስ ነው ጌታዬ (፪x)
ዘላቂ ላልሆነው ለጊዜያዊው ደስታ
እራሴን አላቀርብም ለሚያልቀው በዋይታ
በመጠበቂያዬ ላይ እርሱን እጠብቃለሁ
አይቀርም ይመጣል ጌታን አምነዋለሁ
አዝ፦ ለእኔ መሞቱን ለእኔ መሞቱን (፬x)
አሁን አውቄያለሁ የሚረባኝን
በኑሮዬ ሁሉ ላይ መሾም ያለብኝን
የእኔ መጀመሪያ ብሎም መጨረሺያዬ
ከምንም ከማንም በላይ ኢየሱስ ነው ጌታዬ (፪x)




Meskerem Getu - Eketelehalehu
Album Eketelehalehu
date de sortie
10-09-2014




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.