Teddy Afro - Afralehu текст песни

Текст песни Afralehu - Teddy Afro



ጉድ ያረገኝ ዓይኔ ነው
ኣይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ
ሰው ቢያስተዋውቀን
ኣሳፍረሽኝ መውደዴን
ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ
የማይገባሽ ፍቅር
እንኳን ተናግረሽኝ በሰው ፊት
ዓይንኣፋር ነኝ እኔ ከበፊት
ደፍሬ ባወራሽ አንቺን ብቻ
አደረግሽኝ የሰው መዛበቻ
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህጻን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
ስፈራ ስቸር አናግሬሽ
ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ
ስፈራ ስቸር አናግሬሽ
ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ)
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ)
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም ዓይንአፋር ነኝ
(እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ)
ድሮም ዓይንአፋር ነኝ
ጉድ ያረገኝ ዓይኔ ነው (ኣሃሃ)
ኣይቶሽ በክፉ ቀን
እንድግባባሽ ፈልጌ
ሰው ቢያስተዋውቀን
ኣሳፍረሽኝ መውደዴን
ልነግርሽ ብሞክር
ምን ጨካኝ ነሽ የማትራሪ
የማይገባሽ ፍቅር
ሰው ቢያደፋፍረኝ እንድነግርሽ
ብዬ አሸንፎኛል በቃ ፍቅርሽ
ገና ሳይሽ ጠፋኝ ምገባበት
ፊት ነሳሽኝ እና ሰው ባለበት
ስንት ቆንጆ አለፈኝ እስከዛሬ
ቀርቦ ለማናገር በማፈሬ
ዛሬ አንቺን ብጠይቅ ቃል ቢወጣኝ
ልክ እንደ ህጻን ልጅ አይንሽ ቀጣኝ
ስፈራ ስቸር አናግሬሽ
ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለጼ ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ
ስፈራ ስቸር አናግሬሽ
ምነው መለስሽኝ አሳፍረሽ
ፍቅሬን መግለጼ ምን ክፋት አለው
ተይ ፊት አትንሽኝ ባክሽ አፍራለሁ
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ (ኧረ ተይ)
ተይ ፊት አትንሽኝ አፍራለሁ
ተይ እዳ ኣሃሃ
እንኳንስ ፊት ነስተሽኝ
ድሮም ዓይንአፋር ነኝ



Авторы: Teddy Afro


Teddy Afro - Arifzefen Singles Collection, Vol. I
Альбом Arifzefen Singles Collection, Vol. I
дата релиза
28-02-2014




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.