Songtexte




ወርወር ሲል ዓይኔ ካይኑ ካንድም ሁለት ሦስቴ
ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ድንገት ልጁን በማየቴ
ሳልወድ አስገድዶኝ ተስቤ ወደ እሱ
ይሄው በሄድኩበት እኔ ማውራት ነው ስለሱ
ወርወር ሲል ዓይኔ ካይኑ ካንድም ሁለት ሦስቴ
ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ድንገት ልጁን በማየቴ
ሳልወድ አስገድዶኝ ተስቤ ወደ እሱ
ይሄው በሄድኩበት እኔ ማውራት ነው ስለሱ
ሰረቅ ሰረቅ ሳይነካኝ ሰረቅ ሰረቅ በእጁ ሰረቅ ሰረቅ
በዓይኑ ብቻ ያውቅበታል ልጁ
ሰረቅ ሰረቅ ሳጣራ ሰረቅ ሰረቅ ሳውቅበት ሰረቅ ሰረቅ
ለካስ ልጁ ብዙ ክስ አለበት
እንዴት ልጠብቀው ልቤን
ፍቅር ከወሰደው ቀልቤን
እራሴን ካጣሁት እንዲ ባንዴ
ዉስጤ ከገባህ ካንጀት ሆዴ
ሮጬ የት ላመልጥ በምን ዘዴ
በቃ ፈላ ጉዴ
ጉዴ በቃ ፈላ ጉዴ(፪)
ጉዴ ነው በቃ ከአሁን ወዲ ጉዴ ነው በቃ ልቤ
ጉዴ ነው በቃ የለም ጠፍቶ ጉዴ ነው በቃ ቀልቤ
ጉዴ ነው በቃ እኔንጃለት ጉዴ ነው በቃ ልቤ
ጉዴ ነው በቃ የለም ጠፍቶ ጉዴ ነው በቃ ቀልቤ
ሰረቅ ሰረቅ(፫)
ወርወር ሲል ዓይኔ ካይኑ ካንድም ሁለት ሦስቴ
ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ድንገት ልጁን በማየቴ
ሳልወድ አስገድዶኝ ተስቤ ወደ እሱ
ይሄው በሄድኩበት እኔ ማውራት ነው ስለሱ
ሰረቅ ሰረቅ ሳርይካኝ ሰረቅ ሰረቅ በእጁ ሰረቅ ሰረቅ
በዓይኑ ብቻ ያውቅበታል ልጁ
ሰረቅ ሰረቅ ሳጣራ ሰረቅ ሰረቅ ሳውቅበት ሰረቅ ሰረቅ
ለካስ ልጁ ብዙ ክስ አለበት
ነገር በዓይን ይገባል ነበር ጥንትም ወግና ተረቱ
ፍቅር ቀይሮ ገልጽ አመሉን የስው አያያዙን ትቶ ውሉን
ባይን ከገባ እንዲ ባንዴ
በቃ ፈላ ጉዴ
ጉዴ በቃ ፈላ ጉዴ
ጉዴ በቃ ፈላ ጉዴ
ጉዴ ነው በቃ ከአሁን ወዲ ጉዴ ነው በቃ ልቤ
ጉዴ ነው በቃ የለም ጠፍቶ ጉዴ ነው በቃ ቀልቤ
ጉዴ ነው በቃ እኔንጃለት ጉዴ ነው በቃ ልቤ
ጉዴ ነው በቃ የለም ጠፍቶ ጉዴ ነው በቃ ቀልቤ
ሰረቅ ሰረቅ ሰረቅ ሰረቅ(፪)
ሰረቅ ሰረቅ ሰረቅ ሰረቅ(፪)



Autor(en): Samuel Alemu, Rahel Getu


Attention! Feel free to leave feedback.
Wird geladen
Wird geladen