iMajik - Endegena Songtexte

Songtexte Endegena - iMajik




የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የሚሆነውን አናቅምና
ዛሬ አይመጣ ወይ እንደገና
የሚሆነውን አናቅምና
ነገ አይደለ ወይ ትላንትና
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የነገን ነገር ኧረሚያቅ የለምና
የዛሬን እየው እስቲ በልና ዘና
ኑሮ ሲወቅጠን ልክ እንደ ዘነዘና
የምን ደመና- ጥሩ ዜና ስጠና
ብዙ ሚቀና ሚስጥር አይደል ገመና
ጭንቅላት አሪፍ- ንፁ ነዋ ህሊና
ጠላቴ ፍርክስ- ይበል እንደ ጀበና
እኛ ልንመራ- ኧረ ስንት ዘመናት
ስሜ iMajik መጣው ላሳይ ታምራት
ለዛሬ መኖር ነዋ የኛ ስር-አት
እዚ የደረስኩት ነው ባባቴ ምርቃት
እዚ የደረስኩት ነው በናቴ ምርቃት
ታድያ ሀሳቡ መጥፎ ነገር ሲመጣ
Negative ነገር የሚጨምር ትርታ
እኔ ቀየርኩት ወደ ጥሩ ጨዋታ
የኢትዮጵያ ልጅ ነኝ እኔን የለ ሚረታ
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የሚሆነውን አናቅምና
ዛሬ አይመጣ ወይ እንደገና
የሚሆነውን አናቅምና
ነገ አይደለ ወይ ትላንትና
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
ይደርሳል ኧረ ያለው ከፊታችን
ታድያ እንዴት እንዲ ይጠፋል ተስፋችን
ትበልፅግልን ኢትዮጵያ ሀገራችን
የሷ ደህንነት ሁሌ ሀሳባችን
ኑሮ ቢከፋ, ለደስታ ጊዜ አይጠፋ
ስለምለፋ, አልጠብቅም ወረፋ
እኛ አናቅም መጠየቅ permission
ጊዜማ ያለኝ ለህልምና ለvision
ሌላውን ነገር አደረኩ ከኋላ
ፈጥኖ ለመሞት ኧረ የምን ችኮላ
እኔ አልበገር ይሉኛላ ተኩላ
ቆንጆ ስትመጣ ኧረ ኩሉን ተኩላ
አልኳት ሀሳቡ መጥፎ ነገር ሲመጣ
Negative ነገር የሚጨምር ትርታ
እኔ ቀየርኩት ወደ ጥሩ ጨዋታ
የኢትዮጵያ ልጅ ነኝ እኔን የለ ሚረታ
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የሚሆነውን አናቅምና
ዛሬ አይመጣ ወይ እንደገና
የሚሆነውን አናቅምና
ነገ አይደለ ወይ ትላንትና
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የሚሆነውን አናቅምና
ለቀቅ አድርገው በልማ ዘና
የሚሆነውን አናቅምና
ዛሬ አይመጣ ወይ እንደገና
ወይ እንደገና
ወይ እንደገና
ወይ እንደገና
ወይ እንደገና



Autor(en): Michael Messele Tesfatsion


Attention! Feel free to leave feedback.