Gossaye Tesfaye - Benetelash Lyrics

Lyrics Benetelash - Gossaye Tesfaye



የቀረብኝ ነገር ምን አለ እቴ ከቀናሽኝ በኋላ
ታሪኬ የኋሊት ቢቆጠር ዘመኔ ቢቀመር ቢሰላ
እንደ ፍቅርሽ ታዲያ ምናለ አንጀቴና እና ልቤን ያራሰኝ
ነጠላው ጥበብሽ አይደል ወይ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ
እቴ በነጠላሽ በነጠላሽ (እቴ በነጠላሽ)
እቴ በነጠላሽ በነጠላሽ (እቴ በነጠላሽ)
ተለክፌ በዚያ በጥለቱ (እቴ በነጠላሽ)
አላርፍ አለኝ ልቤ እያነሳሽ
እቴ በምትወጂው በማተብሽ (እቴ በነጠላሽ)
እቴ በአንገትሽ ክር በማተብሽ (እቴ በነጠላሽ)
ምነው በምኩራቡ ሰው ባለበት (እቴ በነጠላሽ)
ብትገጥሚኝ ብገጥምሽ ምን አለበት
ነገር አለኝ ማዶ (አባይ ነው ቤቷ)
ነገር አለኝ ማዶ (አባይ ነው ቤቷ)
ያልቋጨሁት ፍቅር (አባይ ነው ቤቷ)
ሰዶኛል አንድዶ (አባይ ነው ቤቷ)
አባይ ዳር ነው ቤቷ (አባይ ነው ቤቷ)
አባይ ላይ ነው ቤቷ (አባይ ነው ቤቷ)
ለክፋኝ የሄደችው (አባይ ነው ቤቷ)
እቴ በጥለቷ
ሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
አሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
በይ በትከሻሽ (አባይ ነው ቤቷ)
ግጠሚኝና (አባይ ነው ቤቷ)
ጀማው ይፍረደኝ (አባይ ነው ቤቷ)
እኔ ያንቺ ጀግና (አባይ ነው ቤቷ)
ሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
አሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
(አባይ ነው ቤቷ)
(አባይ ነው ቤቷ)
(አባይ ነው ቤቷ)
የቀረብኝ ነገር ምን አለ እቴ ከቀናሽኝ በኋላ
ታሪኬ የኋሊት ቢቆጠር ዘመኔ ቢቀመር ቢሰላ
እንደ ፍቅርሽ ታዲያ ምናለ አንጀቴና ልቤን ያራሰኝ
ነጠላው ጥበብሽ አይደል ወይ ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ
መቼም መላ አታጪ መለኛ ነሽ (እቴ በነጠላሽ)
መች አጣሁሽ እቴ ዘደኛ ነሽ (እቴ በነጠላሽ)
እንደው በማተብሽ አደራሽን (እቴ በነጠላሽ)
እንዳትደርቢብኝ ብርዱን ፈርተሽ
ከሄድሽማ ወዲያ ምን ሊበጀኝ (እቴ በነጠላሽ)
ነገር ቁጭት እንጂ የሚተርፈኝ (እቴ በነጠላሽ)
ምንስ ተቀይሜ ሰው ቢያዝንብሽ (እቴ በነጠላሽ)
በጀም አይል ጀማው አይፍረድብሽ
ነገር አለኝ ማዶ (አባይ ነው ቤቷ)
ነገር አለኝ ማዶ (አባይ ነው ቤቷ)
ያልቋጨሁት ፍቅር (አባይ ነው ቤቷ)
ሰዶኛል አንድዶ (አባይ ነው ቤቷ)
አባይ ዳር ነው ቤቷ (አባይ ነው ቤቷ)
አባይ ላይ ነው ቤቷ (አባይ ነው ቤቷ)
ለክፋኝ የሄደችው (አባይ ነው ቤቷ)
እቴ በጥለቷ
ሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
አሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
በይ ሙክራቡ (አባይ ነው ቤቷ)
ግጠሚኝና (አባይ ነው ቤቷ)
ጀማው ይፍረደኝ (አባይ ነው ቤቷ)
እኔ ያንቺ ጀግና (አባይ ነው ቤቷ)
ሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
አሆናንዬ (አባይ ነው ቤቷ)
(አባይ ነው ቤቷ)



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Album Siyamish Yamegnal
date of release
06-01-2019




Attention! Feel free to leave feedback.