Gossaye Tesfaye - Lagegnish Ande Lyrics

Lyrics Lagegnish Ande - Gossaye Tesfaye



ልክ እንደ አንዱ አካሌ ከቀረሽ በሆዴ
በይላ
በይ ላግኝሽ አንዴ ብትሆኚኝ ገዴ
ፍቅር ሰው ሲይዝ እንዴት ነው አልኩና
ከአንድም ሁለቴ ይዞኛልና
ምን እንደማደርግ ለኔ ባይገባኝም
አቤት ጭንቄ ፋታ እንኳን አልሰጠኝም
ሁሉም እንደኔ እየመሰለኝ
እጠይቃለሁ እስከሚደክመኝ
ምላሽ አጥቼ አረፍ ከማለቴ
መጣች ደሞ ባሳብ ባከላቴ
ዋላታ ሲርባ
አላስተዋለሽ አይኔ ደጋግሞ
እንዲ በአንድ ቀን የቀረው ታሞ
አንቺ ነሽ እንዴ ከፍቅር ጌታ
የተሰጠሽኝ የኔ ስጦታ
በል ድፈር ልቤ እሷን ተጠጋ
አታገኛትም ካልከፈልክ ዋጋ
ገና በግዜ ከፈራህማ
ቀን አይወጣልህ ያለ ጨለማ
ላግኝሽ አንዴ
ላግኝሽ አንዴ
አፌ ለልብሽ እስኪ ያውራ ላንዴ
ሌትም በህልሜ አንቺን ሳወጋ
ምነው ቢያረገው ቀን በዓይነ ስጋ
ያንቺስ የወግነው ኩራት እፍረትሽ
ቆይ ምን ይሉተል የኔን ፍርሀት
ላግኝሽ አንዴ
ላግኝሽ አንዴ
አፌ ለልብሽ አስኪ ያውራ ላንዴ
አንዴ
ኦሆሆ
አሀሀ
ኦሆሆ አሀሀ
አንዴ
ኦሆሆ
አሀሀ
ኦሆሆ አሀሀ
ፍቅር ሰው ሲይዝ እንዴት ነው አልኩና
ከአንድም ሁለቴ ይዞኛልና
ምን እንደማደርግ ለኔ ባይገባኝም
አቤት ጭንቄ ፋታ እንኳን አልሰጠኝም
ሁሉም እንደኔ እየመሰለኝ
እጠይቃለሁ እስከሚደክመኝ
ምላሽ አጥቼ አረፍ ከማለቴ
መጣች ደሞ ባሳብ ባከላቴ
ኦኦኦኦ
ካልታደልክበት ቀድመህ በቦታው
እንቆቅልሹን መቼም አትፈታው
ቀርበህ ጠይቃት ውስጤ አታመንታ
በፍቅር ጉዳይ የለም ይሉኝታ
ኤኤኤ
አሳየኝ አልኩት ከህልሜም በላይ
የልብሽ ፍቃድ ሲሆን በኔ ላይ
ወዶ ሊያነግስሽ አይደለም እንዴ
ፍችው ምኞቴን አግኝቼሽ አንዴ
ላግኝሽ አንዴ
ላግኝሽ አንዴ
አፌ ለልብሽ እስኪ ያውራ ላንዴ
ሌትም በህልሜ አንቺን ሳወጋ
ምነው ቢያረገው ቀን በዓይነ ስጋ
ያንቺስ የወግ ነው ኩራት እፍረትሽ
ቆይ ምን ይሉተል የኔን ፍርሀት
ላግኝሽ አንዴ ኦሆሆ
ላግኝሽ አንዴ አሀሀ
አፌ ለልብሽ ኦሆሆ
እስኪ ያውራ ላንዴ. አሀሀ
አንዴ
ኦሆሆ
አሀሀ
ኦሆሆ አሀሀ
አንዴ
ኦሆሆ
አሀሀ
ኦሆሆ አሀሀ



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Siyamish Yamegnal
Album Siyamish Yamegnal
date of release
06-01-2019




Attention! Feel free to leave feedback.