Jossy Kassa - Teneshina Abrie Lyrics

Lyrics Teneshina Abrie - Jossy Kassa




ብርሃንሽ ወጥቷልና ኢትዮጵያ
አዝ፦ ተነሺና አብሪ
የሃያላን የታላቅ ሀገር ታሪክሽ
የተስፋ ቃል የወንጌልም ዘር ያለብሽ
ሰላምሽ ርቆ ብዙ ደም ፈሶብሻል
የስልጣኔ መጨረሻ ተብለሻል
የመከራ ሌሊትሽ ነጋ በርሱ ጊዜ
የምታበሪበት ዘመን ነው የሕዳሴ
ኢትዮዽያ ኢትዮዽያ
የከፍታ ዘመንሽ ሆነልሽ
አዝ፦ ተነሺና አብሪ
ብሎም ለአፍሪካ ደሞም ለአውሮፓ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ
ብርሃንሽ ወጣ ትንሳኤሽ መጣ ክብርሽን አዩ
የፈጣሪሽ ፊት ወዳንቺ ዞረ ልብሽ ተመልሶ
ሁሉም እንዲያይሽ እንድታበሪ እጅሽን ይዞ
አዝ፦ ተነሺና አብሪ
የፖለቲካ የኢኮኖሚ ቀውስ ሁሉ
ከሠማይ ትእዛዝ ሲወጣ ሰላም ሆኑ
ዘረኝነትና ጥላቻ ቦታ አጣ
የፍቅር መንፈስ ሕዝቡን ሁሉ ይዞ መጣ
የዘንዶውን ራስ አምላክሽ ቀጥቅጦታል
አዝመራሽ ሁሉ ተባርኳል ፈውሶሻል
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
የከፍታ ዘመንሽ ሆነልሽ
አዝ፦ ተነሺና አብሪ
ብሎም ለአፍሪካ ደሞም ለአውሮፓ ለአለም ሕዝቦች ሁሉ
ብርሃንሽ ወጣ ትንሳኤሽ መጣ ክብርሽን አዩ
የፈጣሪሽ ፊት ወዳንቺ ዞረ ልብሽ ተመልሶ
ሁሉም እንዲያይሽ እንድታበሪ እጅሽን ይዞ
አዝ፦ ተነሺና አብሪ
በረሃብ በስደት ሕዝብሽ ተበትኖ
ሲናቅ ሰው ሃገር የሰቀቀን ኑሮ
የናቁሽ ሁሉ የተጠየፉሽ
ጊዜው ሲመጣ ይኸው ሠገዱልሽ
ቀና በይ ከእንግዲህ
ቀና በይ ጊዜሽ ነው
ቀና በይ አትፍሪ
ቀና በይ አብሪ



Writer(s): Simone Tsegay


Jossy Kassa - Teneshina Abrie, Vol. 2
Album Teneshina Abrie, Vol. 2
date of release
23-11-2010



Attention! Feel free to leave feedback.
//}