Mahmoud Ahmed - Teresash Woy Lyrics

Lyrics Teresash Woy - Mahmoud Ahmed



እንደምን ይወድቃል እንደዘበት
ያደረግነው ሁሉ በልጅነት
ፍቅር እንደፈሳሽ ይሆናል ወይ
ለምን ዘነጋሽ ተረሳሽ ወይ
ተረሳሽ ወይ ተረሳሽ ወይ
ኃያል የነበረው ደማቁ ፍቅራችን /አሃ.ሃ ኦሆ/
ድሮ የኖርንበት ደሳሳ ጎጆ'ችን /አሃ.ሃ ኦሆ/
አብረን ያደግንበት እንዴት ይረሳሻል /አሃ.ሃ ኦሆ/
እንዴት ይረሳሻል እንዴት ይረሳል /አሃ.ሃ ኦሆ/
ተረሳሽ ወይ ተረሳሽ ወይ
እንደምን ይወድቃል እንደዘበት
ያደረግነው ሁሉ በልጅነት
ፍቅር እንደፈሳሽ ይሆናል ወይ
ለምን ዘነጋሽ ተረሳሽ ወይ
ተረሳሽ ወይ /አሃ.ሃ/ ተረሳሽ ወይ
አይቻልም 'ንጂ ቢወራ ሊታመን /አሃ.ሃ ኦሆ/
ካንች ጋራ ሆኘ የሳለፍኩት ዘመን /አሃ.ሃ ኦሆ/
ብናቆየው ታሪክ ቢያልፍም ትዝታ ነው /አሃ.ሃ ኦሆ/
እንደዝህ በከንቱ መች የሚረሳ ነው /አሃ.ሃ ኦሆ/
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል
ተረሳሽ ወይ
/ተረሳሽ ወይ/
/ተረሳሽ ወይ/
/ተረሳሽ ወይ/
እንደምን ይወድቃል እንደዘበት
ያደረግነው ሁሉ በልጅነት
ፍቅር እንደፈሳሽ ይሆናል ወይ
ለምን ዘነጋሽ ተረሳሽ ወይ
ተረሳሽ ወይ /አሃ.ሃ/ ተረሳሽ ወይ
ባንበላም ባንጠጣም በባዶ ሆዳችን /አሃ.ሃ ኦሆ/
የጋለ ነበረ የጥንቱ ፍቅራችን /አሃ.ሃ ኦሆ/
ሁሉንም በልብሽ ይዘሽ እያወቅሽው /አሃ.ሃ ኦሆ/
በምን ነገር ይሁን አሁን የረሳሽው /አሃ.ሃ ኦሆ/
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል
ተረሳሽ ወይ
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል
ረሳሽው ወይ
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል
ተረሳሽ ወይ
እንዴት ይረሳል እንዴት ይረሳል
ተረሳሽ ወይ



Writer(s): Nadav Haber


Mahmoud Ahmed - The Best Of... Tizita Vol. 1
Album The Best Of... Tizita Vol. 1
date of release
18-03-2008




Attention! Feel free to leave feedback.