Mahmoud Ahmed - Yenuro Metenshin Lyrics

Lyrics Yenuro Metenshin - Mahmoud Ahmed



የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
አሀሀ እንቅልፍ እየነሳ
አሀሀ ጎትጉቶ ጎትጉቶ
አሀሀ ፍቅርሽ ነው ያመጣኝ
አሀሀ ወዳንቺ ጎትቶ
አሀሀ በውበትሽና በጠባይሽ እንጂ
አሀሀ አይደለም በሀብትሽ
አሀሀ ምናልባት ገብቶሽ ብትረጂ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
አሀሀ ሀብቱንማ እኔና
አሀሀ አንቺ ከተስማማን
አሀሀ የለፈንበትን
አሀሀ ማነው የሚቀማን
አሀሀ ባልደከሙበት ሀብት
አሀሀ ሰማይ የነበሩ
አሀሀ አይተሽ የለ ታጥፈው
አሀሀ ወድቀው ሲሰበሩ
አሀሀ ስለዚህ የኔ ፍቅር
አሀሀ ፍጽም ይቅርብሽ
አሀሀ አይዞሽ አታስቢ
አሀሀ በእኔ ይሁንብሽ
አሀሀ ፍቅር እኔና አንቺ
አሀሀ እምሀል ቤት ይዘን
አሀሀ መኖር እንችላለን
አሀሀ በደስታ ፈንጥዘን
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
አሀሀ እንቅልፍ እየነሳ
አሀሀ ጎትጉቶ ጎትጉቶ
አሀሀ ፍቅርሽ ነው ያመጣን
አሀሀ ወዳንቺ ጎትቴ
አሀሀ በውበትሽና
አሀሀ በጠባይሽ እንጂ
አሀሀ አይደለም በሀብትሽ
አሀሀ ገብቶሽ ብትረጂ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
የኑሮ መጠንሽን ከእኔ ጋር አትለኪ
በዘመዶችሽ ሀብት ይቅር አትመኪ
ኡሁሁይ ሁሁሁሁሁሁ



Writer(s): Traditional


Mahmoud Ahmed - The Best Of... Tizita Vol. 1
Album The Best Of... Tizita Vol. 1
date of release
18-03-2008




Attention! Feel free to leave feedback.