Rophnan - Tesfa Lyrics

Lyrics Tesfa - Rophnan



ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬም ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም
እልፍ ሲሄድ እልፍ ይመጣል (ይመጣል)
እልፍ ወስዶ እልፍን ይሰጣል (ይሰጣል)
አመስጋኝ ሰው ላጣም ላገኘው (ላገኘው)
ተስፋን ስንቅ አድርጎ ይይዛታል
ብርርርር ይላል ልቤ ገና
ሁሉን አልፎ ቀና
ይበራል ልቤ ወጥቶ ከላይ
ተስፋው ነው ከሰማይ
የያዝኩት ወድቆ ቢረግፍም
ብንን (ብንን) ትንን የቀናው ጥምም
ቢልም እድል ካልሆነው ጋር ዝምም (ዝምም)
ምንም እጅ የለም ምንም ′ምሰጠው
እነሳለሁ ደግሜ ነገን ቀድሜ
ስወድቅም እነሳለሁ ደግሜ (ደግሜ ደግሜ ደግሜ)
ራሴን ሸልሜ
ፍሬ ከአፈር ይወድቃል
ቀን ጠብቆ ኖሮ ከዚያች ትንሽ ፍሬ ዛፍ ይነቃል
ላባ ቀለም ይነክራል
የጠቢብ ሰው ስራ በትንሽ ብራና ሃገር ይመክራል
ግንበኛ የናቀው ድንጋይ
ማዘኑን ይተው ተመርጧል ሊውል ከማዕዘኑ ላይ
መዳን አለ በስቃይ
መጥፋት አለ በደስታ መልካም ብቻ እርሱ የባረከው ሰማይ
ወሸታም አለኝ በውሸት ቀለም ሥዕል ስሎ
በውሸት ምሎ
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም (የልቤ ፍም)
አልጠፋችም ዛሬም ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም
ሲሆን ሲሆን ሲሆን የቀና ሲሆን
ሲሆን ሲሆን ደስታ ነው ሃሳብ ሲሳካ ሲሆን
ሲሆን ሲሆን ደስታ ነው ሃሳብ ሲሳካ ሲሆን
(ያዝልኝ ያዝልኝ ያዝልኝ ያዝልኝ)
ገባሁ ቼ!
ደሃ እናት ተስፋን በልጇ አየችው (አየችው አየችው በልጇ አየችው)
ተስፋዋ ልጇ ቢሆን (ተስፋዋ ልጇ ቢሆን ተስፋዋ ልጇ ቢሆን)
አንድ ዓመት ሳይሞላው "ተስፋዬ" አለችው ("ተስፋዬ" አለችው "ተስፋዬ" አለችው)
"ተስፋዬ" አለችው ስሙን (ተስፋዬ ተስፋዬ)
ተስፋ ያድጋል ተስፋ ሆኖ
ተስፋ ይመረቃል ጉልበት ስሞ
ጉልበቷ የተሳመው የተስፋዬ እናት
ተመስገን አለች ተስፋን ለሰጣት
ሮፍናን ተስፋን ላይጥል ነው ያዘለው
የስኬት ሚስጥሩ መንገድ አንድ ነው
መፅናት ራስን ለማንሳት ቁልፍ ነው
ያኔ ተራራው ይናዳል ዝርግ ነው
ስኬት ሲደርሱ መች አለቀና
በማግኘት ውስጥም ማጣት አለና
ጎበዝ ይለኛል ይህ ዓለም ሲዋሽ
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም (የልቤ ፍም)
አልጠፋችም ዛሬም ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም (ይዣት አለቅም)
ዓለም ውሸታም
Yeah ውሸታም ዓለም
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ሮፍናን Bless



Writer(s): Rophnan


Rophnan - Tesfa
Album Tesfa
date of release
24-12-2021

1 Tesfa




Attention! Feel free to leave feedback.