Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Marena-Wotetea paroles de chanson

paroles de chanson Marena-Wotetea - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



እንዴት ብዬ ልግለፀው ላንተ ያለኝን ፍቅር
ቃላቶች አልበቁኝም ሺህ ቅኔ ብደረድር
ከልቤ ወድሀለው የኔ አለም በማይለወጥ ፍቅር
በንጉስ ባገር
ውዴ የኔ ባትሆን ኖሮ ምን ይበጀኝ ይሆን
መቼም እግዜር ጥሎ አይጥልም አውቆ ሠጠኝ አንተን
ይመስገነው እላለሁ ይመስገን
ሰቶኛል ወዳጅ ውዴ አንተን
ባገሩ በከተማው ለልቤ ተመርጠሀል
ከዚህ ወዲያ መውደድ ለማን ሰው ይገኛል
በልቤ ተመላለስ ለፍቅር ለመውደድ
ቃላት በማይገልፁት በእውነት መንገድ
ከልቤ ወድሀለው የኔ አለም በማይለወጥ ፍቅር
በንጉስ ባገር
እንዴት ብዬ ልግለፀው ላንተ ያለኝን ፍቅር
ቃላቶች አልበቁኝም ቅኔ ብደረድር
ከልቤ ወድሀለው የኔ አለም በማይለወጥ ፍቅር
በንጉስ ባገር
ጨረቃ ማለችልኝ ከዋክብት ተገዘቱ
አይኖችህ ቃል ገቡልኝ ፍቅርን ወተወቱ
ይወደኝ አይወደኝም እያልኩኝ ስደናበር
አይኖችህ ቃል ገቡልኝ አስረዱኝ በዝርዝር
ከልቤ ወድሀለው የኔ አለም በማይለወጥ ፍቅር
በንጉስ ባገር
መናዬ ነህ ለልቤ ወዳጄ የኔ ባለቤት
ያንደበትህ ለዛ ለነፍሴ ማርና ወተት
መናዬ ነህ ለልቤ ወዳጄ የኔ ባለቤት
ፍቅርህ የወይን ጠጅ ጠጥቼው ለሰለሰ አንጀቴ




Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gold & Wax




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.