Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Ambasale paroles de chanson

paroles de chanson Ambasale - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



እንከን የሌለበት ከእግር እስከ እራሱ
መተኪያ የሌለው ለስጋ ለነፍሱ
አገኘሁ አንድ ልጅ አገኘሁ አንድ ሰው
አገኘሁ አንድ ሰው አንድ ሰው
መተኪያ የሌሌለው
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣ
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣ
አንተ ያገሬ ልጅ የአምባሰል ጉብል
አንተ ያገሬ ሰው የአምባሰል ጉብል
ማልኩኝ በጎፈሬህ የኔ ጠንበለል
ማልኩኝ በጎፈሬህ ማልኩልህ የኔ ጠንበለል
እንከን የለበትም ምን ይወጣለታል
እንከን የለበትም ምን ይወጣለታል
ሸጋው ያገሬ ልጅ ውበት ፈሶበታል
ሸጋው ያገሬ ልጅ ሸጋው ውበት ፈሶበታል
አክሱም ላሊበላን የፈጠረን ሰው
ጥበበኛ ነው ስል በጣም ሳደንቀው
ሰውን የፈጠረ ፈጣሪን ዘንግቼ
ውበት አሳሰበኝ ይሄን ልጅ አይቼ
ምንድን ነው መለኪያው የሰው ልጅ ውበት
የሰሙትን ሰምተው አይተው ካልወደዱት
እንደ እቃ ተሰፍሮ ሰው ይለካል ወይ
የዚህ ልጅ ሰውነት ከሚዛን በላይ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
ጥንትም አንተን ነበር ከቤቴ ስወጣ
እግሬ የተጓዘው ፍለጋ የወጣ
እግሬ የተጓዘው ወዳ'ንተ ፍለጋ የወጣ
ሽጋው ያገሬ ሰው ሰውነት የኔ አለም
ሰው ባንተ ይለካ ካንተ በለይ የለም
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ካገሬ ልጅ ፍቅር
አንተ ያገሬ ልጅ እኔ እወድሃለው
በልቤ ገብተሀል እምልልሀለው
ልቤ ፈሶልሀል እንደ ወንዝ ጅረት
ብትሻኝ ጠጣ ከፍቅሬ ወተት
ሸጋው ያገሬ ሰው ሰውነት የኔ አለም
ሰው ባንተ ይለካ ካንተ በላይ የለም
ሸጋው ያገሬ ሰው ሚዛኑ ሚዛኑ
እስቲ ሰወች ሁሉ ባንተ ይመዘኑ
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ከዚህ ሰው ፍቅር
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ሸግዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ሸግዬ
ሸጋው ያገሬ ሰው ሚዛኑ ሚዛኑ
እስቲ ሰወች ሁሉ ባንተ ይመዘኑ
ልቤ ፈሶልሀል እንደ ወንዝ ጅረት
ብትሻኝ ጠጣ ከፍቅሬ ወተት
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ካገሬ ልጅ ፍቅር
አንተ ያገሬ ሰው እኔ እወድሃለሁ
በልቤ ገብተሀል እምልልሀለው
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ሸግዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ ሸግዬ
ልቤ ፈሶልሀል እንደ ወንዝ ጅረት
ብትሻኝ ጠጣ ከፍቅሬ ወተት
ሽጋው ያገሬ ሰው ሰውነት የኔ አለም
ሰው ባንተ ይለካ ካንተ በለይ የለም
ሸጋው ያገሬ ሰው ሚዛኑ ሚዛኑ
እስቲ ሰወች ሁሉ ባንተ ይመዘኑ
ደማምዬ ደማምዬ
ደማምዬ
ከበሮውን ምቱት በገናም ይደርደር
ምንም አይለየኝም ካ'ገሬ ልጅ ፍቅር



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gold & Wax




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.