Teddy Afro - Germawineto paroles de chanson

paroles de chanson Germawineto - Teddy Afro



አልሄድ አልሄድ አልሄድ እያለኝ
ልቤ እየተነሳ
አሃ! ልቤ እየተነሳ
ምሎ ምሎ ምሎ ሲገዘት
በይሁዳ አንበሳ
አሃ! በይሁዳ አንበሳ
አጋር ብልህ አጋር ሥዩመ እግዚአብሄር ዘእምነገደ
ንጉሥ ቀዳማዊ
አሃ! ንጉሥ ቀዳማዊ
አለኝ አለኝ አለኝ ታሪካቸው
ድር ቢያብር ሆነን አፍሪካዊ
አሃ! ሆነን አፍሪካዊ
ጁዳ አንበሳ ኪሎ
ቢቀጥልም ኪሎ
ጥላ ሆነ ትልቅ ዋርካ
ለአንድነቷ ለአፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉሥ ጁዳ አንበሳ
ቀዳማዊ ጁዳ አንበሳ
ግርማዊነትዎ የሕዝብ እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ኃይለሥላሴ
ግርማዊነትዎ የሕዝብ እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ኃይለሥላሴ
ጆሞ ጆሞ ጆሞ ኬንያታ
ከንኩሩማ መክረው ከግርማዊ
አሃ! መክረው ከግርማዊ
አርበኛ የጥቁር ንጉሥ ሞገስ ለአፍሪካ
እነ ኩዋሜ ሆኑ ቀዳማዊ
አሃ! ሆኑ ቀዳማዊ
አብሮ የመኖር ሁሉን የሚፈታው
ታላቅ ህልም የነበራቸው
አሃ! ህልም የነበራቸው
አጋር ብልህ አጋር ሥዩመ እግዚአብሄር
ዘእምነገደ ግርማዊነታቸው
አሃ! ግርማዊነታቸው
ጁዳ አንበሳ ኪሎ
ቢቀጥልም ኪሎ
ጥላ ሆነ ትልቅ ዋርካ
ለአንድነቷ ለአፍሪካ
እነ ጆሞ ኬንያታ
የኖራቸው ትልቅ ቦታ
ከተፈሪ መክረው ለካ
ተሞከረ ፓን አፍሪካ
አራዳ ታቦቱ በፒያሳ
ቀዳማዊ ንጉሥ ጁዳ አንበሳ
ቀዳማዊ ጁዳ አንበሳ
ግርማዊነትዎ የሕዝብ እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ኃይለሥላሴ
ግርማዊነትዎ የሕዝብ እንደራሴ
የአፍሪካ አባት ኃይለሥላሴ
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!
ራስተፈራይ!



Writer(s): Teddy Afro


Teddy Afro - Abugida
Album Abugida
date de sortie
01-06-2001




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.