Текст песни




ትላንትና ታሪክ ነገ ደግሞ ሚስጥር
ዛሬ ስጦታ ነው አሁን ደግሞ ጠንክር
የከፋ ቢመስልም ያለፍክበት ችግር
አታስብ ያልፋል ይሄም ማያልፍ የለም በምድር
ይሄም ያልፋል
ያልፋል
ይሄም ያልፋል ያልፋል
ሚረዳህ ያጣህ ቢመስልህም
ብቻህን አደለህም
እኔ አለው ከጎንህ ጭንቀት አይበጅህም
እጅህን ባልይዝም ጥዬህ ግን አልሄድም
በርታ ቢደክምህም መቻል ነው ግድ የለም
ይሄም ያልፋል
ያልፋል
ይሄም ያልፋል ያልፋል
ትላንት ያደረከው አንተን አይገልህም
ዛሬ ላይ ነህ አሁን የነገህን ቀምም
የከፋ ቢመስልም ያለፍክበት ችግር
አታስብ ያልፋል ይሄም ያልፋል ይሄም
ሳይጨልም አይነጋም
ይሄም ያልፋል
ያልፋል
ያልፋል ያልፋል
ዛሬ ስጦታ ነው አሁን ደግሞ ጠንክር
የከፋ ቢመስልም ያለፍክበት ችግር
አታስብ ያልፋል ይሄም ማያልፍ የለም በምድር
End





Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка