Текст песни




መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ
ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ካንቺ በላይ ዕዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ
ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ካንቺ በላይ ዕዉቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
ለኔው ጥቅም በኔው
ሰው ተመክሬ
አላውቅም አድምጬ
ከልብ አምርሬ
አሁን ለምን ገባኝ
ባንቺ ስመከር
ያሉኝን ብለሺኝ
የምፍጨረጨር
ከኔ ነው ወይ ካንቺ ነው
ልቤን ለእጅሽ የሰጠነዉ
ማኩረፍ የኔ ነበር
አልሸፋፈንኩም
ካንቺ ጀምሬ ግን
አልተቀየምኩም
ምንድነው ብርቅ ሆኖ
የሚያስወድደኝ
ሁሉሽን እንዳደንቅ
የሚያስገድደኝ
የት ብለው የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም ከወደዱ
መልክን የሻረዉ
አንቺ ጋር ምን ተሻለው
ከሩቅ ሳትስቢ
አየሁ ልቤ ስትገቢ
ካንቺ በላይ ቆንጆ ሞልቶ
ያዉቃል ልቤም ቀርቦም አይቶ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ካንቺ በላይ ዕውቀታቸው
ስቄም ነበር በቀልዳቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
ተቀይሯል ዓይኔ
ወዷል መልክሽን
ሲመስሉሽ ያደንቃል
ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ
ያንቺ ዓይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም
እንዳለሽ አቻ
የት ብለው የት ቢሄዱ
መስፈርት የለም ከወደዱ
ተቀይሯል ዓይኔ
ወዷል መልክሽን
ሲመስሉሽ ያደንቃል
ሲቀርቡሽ አንቺን
ቆንጆም ዉብም ለኔ
ያንቺ ዓይነት ብቻ
ባይም ልቤ አያምንም
እንዳለሽ አቻ
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው
ግን በምን በለጥሻቸው
ቆንጆዎቹን አስናቅሻቸው
ዝምታሽ በለጣቸው
ደብዝዘሽ አጋለጥሻቸው



Авторы: Samuel Alemu, Eyob Mekonen


Eyob Mekonen - Ende Kal
Альбом Ende Kal
дата релиза
01-09-2010




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка