Laeke feat. Dagmawit Ameha - Dejen текст песни

Текст песни Dejen - Laeke




እንዴት ነዉ ነገሩ ደጀን ከሠሞኑ
የረጋ የተጋ ሆኗል አኳኋኑ
እንዴት ነዉ ነገሩ ደጀን ከሠሞኑ
የረጋ የተጋ ሆኗል አኳኋኑ
አይኒቱን ሰላቢ እዝን አባራሪ
ንቅሡ አሳሳሉ የገፁ በሃሪ
እንደ ቤተክርስትያን ግድግዳ
እንደ ቤተ እግዚሃሩ
ደጀን ዝም አለና
አወራ ግንባሩ
ህህህህ
ህህህህ
እንዴት ነዉ ነገሩ አረማመድ ፊቱ
አሁንስ አለህ ዎይ እንደ ልጅነቱ?
ወይስ ወለም ይላል ሰንከል አንደበትህ
እግርህስ ረግጧል ዎይ እንድታድግበት?
ሲረጋ ዝም ሲል ድንገት እንደ ዕድሉ
እንደኔዉ ቀበርክ ዎይ ሞተህ በከፊሉ?
መደብ መደርደርያዉ ቁመቱስ ደረስከዉ?
መድሐኒት የት አለ እባብ ለነከሰዉ
ደጀን ትርምሱ መች ያነጋግራል
ህልምና ምኞትስ ከገፉ ይኖራል?
የኔ ሆድ ባሩን ያንተስ እንደምነዉ?
አብረን ባደርንማ እስሩን ባወቅነዉ
እስሩን ባወቅነዉ
እንዴት ነዉ ነገሩ ደጀን ከሠሞኑ
የረጋ የተጋ ሆኗል አኳኋኑ



Авторы: Fikru Semma


Laeke feat. Dagmawit Ameha - Reqiq
Альбом Reqiq
дата релиза
08-08-2023




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
//}