Текст песни




ማርዳ ነው የደረቷ ያንገቷ ጌጥ
ዶቃ ነው ቀለማት ይደመቀ
እንደ ፈትል እንደ ሀገርልብስ
እንደ እናቷ እጅ ውበቷ ረቀቀ
ዜማ ነው ሳቋ ለነፍሴ ሙዚቃ
ፍቅር ነው ለልቤ የሚበቃ
ቆንጆ ናት ልጅት ጥግ ናት
የውብዳር ውበትበሷ ይለካ
እንደ የኔታ ፅሁፍ እንደ ተለቀመው
መልክሽ የእጅ ስራ ውበትሽ እንከን የለው
ስም አለሽ ወይ?
ውቢት ስም አለሽ ወይ?
መሳይሽ የለም ታውቂያለሽ ወይ?
እንኳን ተኩለሽው
እይኖችሽን በውበት ከሽነሽው
BABY እንኳን የክቱን ልብስ
ጥርጥሩን ቀሚስ እንዲህ ዘንጠሽው
ባትኳይም ታምሪያለሽ
መልክ እና ፀባይ
ከውስጥም ሆነ ከላይ
አንቺ ሰው ታምሪያለሽ
ቃልሽ ሀቅ ነው
ሳቅሽ የሙዚቃ ነው
አንቺዬ ታምሪያለሽ
ስትሆኚ እንደልብሽ
ደስ ትያለሽ ትያለሽ
ታምሪያለሽ
ባትኳይም ታምሪያለሽ
ታምሪያለሽ
ይደምቃል ይፈካል አንቺ ያለሽበት
መልከ ብርሀን ይለያል የቆምሽበት
ሲያይሽ ውሎ ዐይኔ ሲያይሽ አደረ
መቼ ጠገበሽ አሻግሮ እያማተረ
ተይ ማነሽ ተይ ማናት እያሉ ያዩሻል
ከሰው መሀል ነጥለው ይለዩሻል
ሰው በፍቅር አንቺን አይቶ ቢወድቅም አይፈረድም
ከቶ ለኔ ይሄ አይደንቅም
ደስ ይላል ደስ ይላል አይንሽ ደስ ይላል
ስትስቂማ መልክሽ ፈክቶ እዩኝ እዩኝ ይላል
ይበቃል ይበቃል ለአለም ይበቃል
ውበትሽ ልዩ ከሴት ሁሉ ይልቃል
ተኩለሽው እይኖችሽን በውበት ከሽነሽው
BABY እንኳን የክቱን ልብስ
ጥርጥሩን ቀሚስ እንዲህ ዘንጠሽው
ባትኳይም ታምሪያለሽ
መልክ እና ፀባይ
ከውስጥም ሆነ ከላይ
አንቺ ሰው ታምሪያለሽ
ቃልሽ ሀቅ ነው
ሳቅሽ የሙዚቃ ነው
አንቺዬ ታምሪያለሽ
ስትሆኚ እንደልብሽ
ደስ ትያለሽ ትያለሽ
ታምሪያለሽ
ባትኳይም ታምሪያለሽ
እንደ የኔታ ፅሁፍ እንደ ተለቀመው
መልክሽ የእጅ ስራ ውበትሽ እንከን የለው
ስም አለሽ ወይ?
ውቢት ስም አለሽ ወይ?
መሳይሽ የለም ታውቂያለሽ ወይ?
እንኳን ታውቂያለሽ ወይ?
እንኳን ታውቂያለሽ ወይ?



Авторы: Rophnan, Rophnan Nuri Muzeyin



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.
Загрузка
Загрузка