The Christians feat. Samuel Negussie - Bezih Alem (feat. Samuel Negussie) текст песни

Текст песни Bezih Alem (feat. Samuel Negussie) - The Christians , Samuel Negussie



በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×)
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤
በአንተ ዘንድ ያለ የህይወት ቃል
ሌላ ስፍራ የትም 'ማላገኘው
ብር የማይሰጠኝ ወርቅ የማይሰጠኝ
የሕይወቴን አቅጣጫ የለወጠው፤
የሁልጊዜ ነው የልቤ ሰላም
ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨው
በዚህ አለም ነገር የማይወሰን
የእኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው
ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ
ብዙ ደስታ አለ፤
ብዙ ሰላም አለ በሕይወቴ
ብዙ ሰላም አለ፤
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ
መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ
ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ
መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ
ሸክም የከበደው ወደ እኔ ይምጣ
ይረፍ ብለህ የጠራኸኝ አንተ እኮ ነህ
ሁሉንም ነገር ለአንተ ሰጥቼ
እፎይ ብዬ ተደላድዬ ምኖርብህ
ኢየሱስ ከአንተ ጋር ያለኝ ህብረት
ማለት ለእኔ አለሜ ነው፥ አለሜ ነው
ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት
ምክንያቱ ነው የዘላለሜ የሰመረበት
በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ
ከአንተ ጋር እንደመኖር
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ
እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ
ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×)
ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤
Writer- Mignot Dansa




The Christians feat. Samuel Negussie - Ethiopian Protestant Mezmur, Vol. 6
Альбом Ethiopian Protestant Mezmur, Vol. 6
дата релиза
29-09-2016



Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.