Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Aynama Lyrics

Lyrics Aynama - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



ወፉ ወፉ አይናማ
ወፉ አይናማ አይናማ
ሰዉ ሁሉ አይናማ
ቆንጆ አይናማ
ምኑ ይጠላል የዚህ ከተማ
ወፉ ወፉ አይናማ
ወፉ አይናማ አይናማ
ሰዉ ሁሉ አይናማ
ቆንጆ አይናማ
ምኑ ይጠላል የዚህ ከተማ
እጹብ ነው ድንቅ ነው የዚህ ልጅ ቁንጅና
ይመታ ከበሮ ይደርደር በገና
ውብ ሃገር ውብ ሃገር ውብ እናት አለም
ውለጅ መንታ መንታ ልጅ አይጠገብም
ቆንጆ ቆንጆውን ሸጋ ሸጋውን
የወይንሃረጉን አምጡልኝ ለኔ
ሎጋ ሎጋውን ይወዳል አይኔ
አይኔ አይኔ
አሃ አሃ ቆንጆ ቆንጆውን
አሃ አሃ ሎጋ ሎጋውን
አሃ አሃ ቆንጆ ቆንጆውን
አሃ አሃ ሎጋ ሎጋውን
ወፉ ወፉ አይናማ
ወፉ አይናማ አይናማ
ሰዉ ሁሉ አይናማ
ቆንጆ አይናማ
ምኑ ይጠላል የዚህ ከተማ
ወፉ ወፉ አይናማ
ወፉ አይናማ አይናማ
ሰዉ ሁሉ አይናማ
ቆንጆ አይናማ
ምኑ ይጠላል የዚህ ከተማ
የከተማ ልጅ ነው የአራዳ የአራዳ
አውጡት በአደባባይ አይወደም በጓዳ
ቅርጥፍጥፍ ቅርጥፍጥፍ ወየው በላኝ ጅቦ
በሳቅ በፈገግታ በምላስ ታጅቦ
ቆንጆ ቆንጆውን ሸጋ ሸጋውን
የወይንሃረጉን አምጡልኝ ለኔ
ሎጋ ሎጋውን ይወዳል አይኔ
አይኔ አይኔ
አሃ አሃ ቆንጆ ቆንጆውን
አሃ አሃ ሎጋ ሎጋውን
አሃ አሃ ቆንጆ ቆንጆውን
አሃ አሃ ሎጋ ሎጋውን
ኸረ ጉዴ ፈላ አይን አዋጅ ሆነብኝ
ቆንጆ ሰው በአይኔ ላይ ሞልቶብኝ ሞልቶብኝ
ከማን ተዋድጄ ከማን እጣላለው
ያም ሸጋ ይሄም ሸጋ የቱን እመርጣለው
አምላኬ ንገረኝ አን'ታውቃለህ ለኔ
ልቤ ሰው አይጠላ ገባሁኝ ኩነኔ
የሃገሬ ልጆች እማይጠገቡ
በስለት ተወልደው በስለት አገቡ
ምነው እኔ ብቻ በገበያው ላይ
አላፊ አግዳሚውን ተገትሬ ሳይ
ጸሃዩ አጠቆረኝ አከሳሰለኝ
አደናቅፎት እንኳ አንዱን ቢጥልልኝ
የተሸከምኩትን ቢያቃልልኝ
አሆሆሆ
ሎጋው ቆንጆው
አሆ
ቆንጆነው ሸጋነው
ቆንጆነው ሸጋነው
እናቱ ትውለድ
እናቱ ትውለድ
ትውለድ መንታ መንታ
ትውለድ መንታ መንታ
መንታ መንታውን
አይኑ እንደመትረየስ የሚፋጀውን
አሆ



Writer(s): Shibabaw Ejigayehu


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gigi
Album Gigi




Attention! Feel free to leave feedback.