Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Nafekeñ Lyrics

Lyrics Nafekeñ - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



ናፈቀኝ!
ናፈቀኝ የኛ ቤት ጨዋታ
ቁርስ ምሳ እራቴ የእምዬ ፈገግታ
የዘመድ አዝማዱ ጨዋታ በካካታ
አንተዬ!
የጠላው ቤት ሌላ የጠጁ ቤት ሌላ
ፋሲካው አያልፍም ሰው ጠግቦ ሳይበላ
የመጣዉ እንግዳ ሰክሮ ሳይጣላ
ናፈቀኝ ዛሬ በሰዉ ሃገር ትዝታዉ ገደለኝ
የሰዉ ከብት እያየሁ እያንገበገበኝ
ውሃ ጃሪው ዉሃ ኮሎ ሲሉኝ
ያ'ባቴም በሬዎች የ'ናቴም መሰሉኝ
ኦይ!
ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ
ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ ይላሉ
ውሃ ጃሪ የ'ናቴ በሬዎች ጥጆች
ውሃ ጃሪ ያ'ባቴን ይመስላሉ
ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ
ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ ይላሉ
ውሃ ኮሎ የ'ናቴ በሬወች ጥጆች
ውሃ ኮሎ ያ'ባቴን ይመስላሉ
ስም የለኝም ስም የለኝም በቤቴ
ስም የለኝም ስም የለኝም በቤቴ
አንዱ እምዬዋ ሲለኝ አንዱ ሲለኝ አከላቴ
ጎኔ ሽኳሬ ሲሉኝ
በፍቅራቸዉ ሲጠሩኝ
ናፈቀኝ ጎረቤቱ ናፈቀኝ ጨዋታው
ናፈቁኝ 'ህት ወንድሞቼ አይጠፋም ትዝታው
ናፈቀኝ ደገኛው ቄስ ሞገስ
በፈረስ በበቅሎ ተጉዞ ሲመጣ
ለአመት በዓል ጨዋታ
ሰዉ እልል እያለ ሲቀበል በምቢልታ
አንተዬ'ይ በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
የሀገሩ ገነኛ እያለ ሲመጣ
አባየ ናፈቀኝ የከብቶቹ ጌታ
ሲባርክ ሲመርቅ የቤቱን ጨዋታ
እምየ እናት አለም
ጉልበትሽ ችሎታሽ ይበልጣል ከሺህ ሰው
ያን ሰዉን ሁሉ እጅሽ ያጠገበው
ናፈቀኝ!
ያያ ታዴ ሆዴ
የሽመል አቧራ አይችልም ገላዬ
የኔ ሆድ አሌዋ ቁም ከኋላዬ
አያ ድማሙ አያ ድማሙ
አያ ድማሙ አያ ድማሙ
አባይ ወዲያ ማዶ ትንሽ ግራር በቅላ
ልቤን ወሰደችው ከነስሩ ነቅላ
እያለ ሲዘፍን ትዝታው ገደለኝ
ዛሬ በሰዉ ሃገር
የሰዉ ከብት እያየሁ እያንገበገበኝ
ውሃ ጃሬው ውሃ ኮለል ሲሉ
ያባቴም በሬዎች የናቴም መሰሉኝ
ኦይ!
ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ
ውሃ ጃሪ ውሃ ጃሪ ይላሉ
ውሃ ጃሪ የ'ናቴ በሬዎች ጥጆች
ውሃ ጃሪ ያ'ባቴን ይመስላሉ
ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ
ውሃ ኮሎ ውሃ ኮሎ ይላሉ
ውሃ ኮሎ የ'ናቴ በሬወች ጥጆች
ውሃ ኮሎ ያ'ባቴን ይመስላሉ
ኦሆ!
የቤቱ ጨዋታ የመንደሩ ወሬ
ናፈቀኝ ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ
ዬ-እዬ ዬ-እዎ ኦው-ዬ
ናፈቀኝ ናፈቀኝ ናፈቀኝ ሀገሬ



Writer(s): Ejigayehu Shibabaw


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gigi
Album Gigi




Attention! Feel free to leave feedback.