Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Mengedegna Lyrics

Lyrics Mengedegna - Ejigayehu "Gigi" Shibabaw



ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው (ብነግረው)
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው (ብነግረው)
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ይሻለው ነበረ መውደድ ከተራራ
ጥሎ ከማይሄደው ከማይሸሸው ጋራ
ይሻለው ነበረ መውደድ ከተራራ
ጥሎ ከማይሄደው ከማይሸሸው ጋራ
ተራራው ሰው ሆኖ ከንፈሬን ባይስመው
ተራራው ሰው ሆኖ ጡጤን ባይዳብሰው
ተራራው ሰው ሆኖ አይን አይኑን ባላይ
ፀሀይ እሞቃለው ወጥቼ ከላይ
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው
ፍቅሬ ሆይ እኔ አንተን መውደዴን እንዴት ብዬ ልተው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው (ብነግረው)
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ልቤ አልሰማኝ አለ ብነግረው (ብነግረው)
ልቤ አልሰማኝ አለ ብመክረው
ጎዳናው መንገዱ ሸሽቶኛል ሰላም አርቆ ወስዶኛል
ደሞ አዙሮ አዙሮ ካንተ ያመጣኛል
ተው ልቤ ተው ልቤ ተው ልቤ ተመከር
ከሚበጅህ ወዳጅ ከሚሻልህ
የሽንብራ ቆሎ እንዴት ጣፋጭ ነው
ቆንጥሬ በልቼ ምኑን ልዋጠው
አንት መንገደኛ አንተ መንገደኛ አንተ ደገኛ
አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየው እንቅልፍም አልተኛ
አንት መንገደኛ አንተ ደገኛ
አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየው እንቅልፍም አልተኛ
የሽንብራ ቆሎ እንዴት ጣፋጭ ነው
ቆንጥሬ በልቼ ምኑን ልዋጠው
አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለው
በየትኛው ሰማይ ባልፍ አገኝሃለው
አንት መንገደኛ አንተ ደገኛ
አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየው እንቅልፍም አልተኛ
አንት መንገደኛ አንተ ደገኛ
አትመጣልኝም ወይ አንተን ካላየው እንቅልፍም አልተኛ



Writer(s): Shibabaw Ejigayehu


Ejigayehu "Gigi" Shibabaw - Gigi
Album Gigi




Attention! Feel free to leave feedback.