Teddy Afro - Menta Wodije текст песни

Текст песни Menta Wodije - Teddy Afro



ላላ-ላላ
ላላ-ላላ
ላላ-ላላ
ብንጠቅስ ከሰጠን ከመጽሃፉ
ላንድ ሰው ኣንድ ይላል ምእራፉ
በመንታ መልካቸው መሳቤ
ሁለት ወዶ ለካ ይሆናል ተው ይቅር ልቤ
ይበጅሃል ባንዱ ልብህ አንድዋን ማሰብ
ለመለየት ኣቃተኝ ሳያቸው
ይገርማል አንድ ነው መልካቸው
በመንታ መልካቸው መሳቤ
ሁለት ወዶ ፍቅር አይሆንም ተው ይቅር ልቤ
ይበጅሃል ባንዱ ልብህ አንድዋን ማሰብ
ላላ-ላላ
ለየው እንጂ አምላክ ነፍስዋን
የ'ህትዋ መልክ ቁርጥ እስዋን
ልቤን ወጋው የፍቅር ሰደድ
መንታ ወዶ ካ'ንድ ቤቱ ሁለት
ሰውን መውደድ ምን ክፋት አለው
ግፍ አይደለም ይህን አውቃለው
ወደቅኩ እንጂ ሁለት ወድጄ
እህትዋን ሳይ ለስዋ ሰግጄ
ሄጄ ብላኝ እስዋ
ሄጄ ላየው ቤትዋን
ሄጄ ወድጄያት መጣው
ሄጄ መንታ 'ህትዋን
ሄጄ ብየ ተመልስኩ
ሄጄ ደግሜ አልመጣም
ሄጄ ወይ አፈጣጠር
ሄጄ ይገርማል በጣም
ይገርማል!
ብንጠቅስ ገልጠን ከመጽሃፉ
ላንድ ሰው አንድ ይላል ምእራፉ
በመንታ መልካቸው መሳቤ
ሁለት ወዶ ልክ ኣይሆንም ተው ይቅር ልቤ
ይበጅሃል ባንዱ ልብህ አንድዋን ማሰብ
ሰውን መውደድ ምን ክፋት ኣለው
ግፍ አይደለም ዪሄን ኣውቃለው
ወደቅኩ እንጂ ሁለት ወድጄ
እህትዋን ሳይ ለስዋ ሰግጄ
ለየው እንጂ ኣምላክ ነፍስዋን
የ'ህትዋ መልክ ቁርጥ እስዋን
ልቤን ወጋው የፍቅር ሰደድ
መንታ ወዶ ካ'ንድ ቤት ሁለት
ሄጄ ብላኝ እስዋ
ሄጄ ላየው ቤትዋን
ሄጄ ወድጄያት መጣው
ሄጄ መንታ እህትዋን
ሄጄ ብየ ተመልስኩ
ሄጄ ደግሜ አልመጣም
ሄጄ ወይ አፈጣጠር
ሄጄ ይገርማል በጣም
ይገርማል!
ይገርማል!



Авторы: Teddy Afro


Teddy Afro - Musica Hiwote: Single Collections, Vol. 1
Альбом Musica Hiwote: Single Collections, Vol. 1
дата релиза
01-04-2012




Внимание! Не стесняйтесь оставлять отзывы.