Bereket Tesfaye - Getan Agengehu Songtexte

Songtexte Getan Agengehu - Bereket Tesfaye




ተጭኖብኝ የማልችለውን
የሞት ፍርሀት አርጎኝ ምስኪን
መች አገዝኝ የእኔነት ካባዬ
አልቆ ነበር የመኖር ተስፋዬ
ግን አንድ ቀን ወንጌል ሰማሁኝ
ይታደጋል ያድናል ሲሉኝ
በቅንነት እጄን አነሳሁኝ
የዛች ለት ጌታን አገኘሁኝ
አዲስ ነገር የዛች ለት ሆነ (፪x)
በመንፈሴ ሰላም ሰፈነ (፪x)
አፈሰሰው በልቤ ደስታ (፪x)
መንፈስ ቅዱስ የሰላም ጌታ (፪x)
በአገር በሰፈሩ እታማ ጀመረ
የእናት እና የአባቱን ሃይማኖት ቀየረ
ይህን ያንን ብለው በእኔ ላይ ተነሱ
እኔ የቀመስኩትን ምነው በቀመሱ
ኢየሱስ ብቸኛ አማራጭ የሌለው
ወደ ሰማይ መግብያ ብቸኛ መንገድ ነው
ያዳነኝ ኢየሱስ ነው
የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
በመስቀል ላይ ኢየሱስ ነው
የተወጋልኝ ኢየሱስ ነው
ዋጋ ከፍሎ ኢየሱስ ነው
በደም ገዛኝ ኢየሱስ ነው
ከጻድቃን ጋር ኢየሱስ ነው
የቀላቀለኝ ኢየሱስ ነው
መዘበቻ አርጓት ነፍሴን ሰይጣን ክፉ አይራራ አያዝን
ከሱ ለማምለጥ ብዙ ጣርኩኝ ግን አልቻልኩኝ
በዚህ ሁኔታ ወንጌል ሰማሁኝ እየሱስን ተገናኘሁኝ
ሰው መሆኔን የወደድኩት ያየሁት ለት
የልጅነትን ሥልጣንን ሰጠኝ ሥልጣን ሰጠኝ
ያሳደደኝን አሳደድኩኝ አሳደድኩኝ
የበቀል ቅባት እራሴን ቀባኝ እራሴን ቀባኝ
ያስጨነቀኝን አስጨነኩኝ አስጨነኩኝ
እናንተ ደካሞች ሸክማቹህ ከባድ
ወደ እኔ ያለ ይሄ ሰውን ወዳጅ
ያሳረፈኝ ኢየሱስ ነው
ሰው ያደረገኝ ኢየሱስ ነው
ያከበረኝ ኢየሱስ ነው
ያዘመረኝ ኢየሱስ ነው
ዋጋ ከፍሎ ኢየሱስ ነው
በደም ገዛኝ ኢየሱስ ነው
ከጻድቃን ጋር ኢየሱስ ነው
የቀላቀለኝ ኢየሱስ ነው



Autor(en): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Unknown



Attention! Feel free to leave feedback.