Eyob Mekonen - Yezebarkalu Songtexte

Songtexte Yezebarkalu - Eyob Mekonen




ይዘባርቃሉ
ሳይገባቸው ነገሩ ሁሉ
ከቶ ለምን ፈራሽ
ማንነቴን በደንብ እያወቅሽ
ፍቅርሽ ላይ ያንቺን ጉዳይ
ማን ያውቃል ካንቺ በላይ
አልፈርድም በማያውቁት
ላንቺው ነው ግልፅ የሆንኩት
ይዘባርቃሉ
ሳይገባቸው ነገሩ ሁሉ
ከቶ ለምን ፈራሽ
ማንነቴን በደንብ እያወቅሽ
ፍቅርሽ ላይ ያንቺን ጉዳይ
ማን ያውቃል ካንቺ በላይ
አልፈርድም በማያውቁት
ላንቺው ነው ግልፅ የሆንኩት
እኔ ባንቺ ተክዣለሁ
ብናገር ምን ዋጋ አለሁ
ድሮስ ልቤን ለማን ሰጠው
ጉዳዬስ ከማን ነው?
አንቺው ሰማሽ የመጡትን
ሲያወሩ የማያውቁትን
ቀረብ ብለሽ አስረጅያቸው
ንቀሽ ካልተውሻቸው
አታውሪ ቀድመሽ ለኔ
እያየሽ ሆነሽ ጎኔ
እኔ ባንቺ ተክዣለሁ
ብናገር ምን ዋጋ አለሁ
ድሮስ ልቤን ለማን ሰጠዉ
ጉዳዬስ ከማን ነው?
አንቺው ሰማሽ የመጡትን
ሲያወሩ የማያውቁትን
ቀረብ ብለሽ አስረጅያቸው
ንቀሽ ካልተውሻቸው
ሆድ ባሰኝ እያወቅሽኝ
መሰለኝ አንቺው ያልሽኝ
ይዘባርቃሉ
ሳይገባቸው ነገሩ ሁሉ
ከቶ ለምን ፈራሽ
ማንነቴን በደንብ እያወቅሽ
ፍቅርሽ ላይ ያንቺን ጉዳይ
ማን ያውቃል ካንቺ በላይ
አልፈርድም በማያውቁት
ላንቺው ግልፅ የሆንኩት
ግድ የለብን የማሳመን
ሌሎቹን ለማሳመን
ውሎ ሲያድር ይረዱታል
ኋላ ያፍሩበታል
ውስጥ የሞላው እዉነታችን
ያልፍና ከሁለታችን
የሌሎቹን ይገነባል እኛ ከተግባባን
ያዩታል ያየሽውን
ዝም አይሉም ዝም ያልሽዉን
ግድ የለብን የማሳመን
ሌሎቹን ለማሳመን
ውሎ ሲያድር ይረዱታል
ኋላ ያፍሩበታል
ውስጥ የሞላው እዉነታችን
ያልፍና ከሁለታችን
የሌሎቹን ይገነባል እኛ ከተግባባን
ያዩታል ያየሽውን
ዝም አይሉም ዝም ያልሽዉን
አንድ ቀን ያወሩታል
ለእነርሱ ጊዜ ሞልቷል
አታውሪ ቀድመሽ ለኔ
እያየሽ ሆነሽ ጎኔ
ሆድ ባሰኝ
እያወቅሽኝ መሠለኝ
አንቺው ያልሽኝ



Autor(en): Samuel Alemu, Eyob Mekonen Unknown


Eyob Mekonen - Ende Kal
Album Ende Kal
Veröffentlichungsdatum
12-06-2008




Attention! Feel free to leave feedback.
//}