Bereket Tesfaye - Edmeyen Lyrics

Lyrics Edmeyen - Bereket Tesfaye




ዕድሜዬን በሙሉ ብሰጠው አይቆጨኝም
በመስቀል ደሙን ላፈሰሰልኝ
ሰው ሁሉ ንጹህ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ
በምድር ላይ እኔ ብቻ በኀጢአት ብበላሽ
መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን
ኢየሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር
እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ
ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ
ስለዚህ እኔ አመልካለሁ
ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው
ክፉ አመሌን አይቶ ከቶ ያልሰለቸው
አስቸጋሪ ባሕሪዬ ልቡን ያላራደው
በፍቅሩ አሸነፈኝ የራሱ አደረገኝ
የማይገባኝን ክብር አለበሰኝ
እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ
ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ
ስለዚህ እኔ አመልካለሁ
ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው
ዕድሜዬን በሙሉ ብሰጠው አይቆጨኝም
በመስቀል ላይ ሞቶ ራሱን ለሰጠኝ
አዋርዳለሁኝ ሁለንተናዬን ለእርሱ
ዳግም ወዶኛልና ኢየሱስ ንጉሡ
የፍቅር ትርጉም የገባዉ
ኧረ ማነው ሚገልጸዉ
የአፍቃሪ ትርጉም ማነው እርሱ
ኢየሱስ ያልራራ ለነፍሱ
እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ
ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ
ስለዚህ እኔ አመልካለሁ
ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው
ሰው ሁሉ ንጹህ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ
በምድር ላይ እኔ ብቻ በኀጢአት ብበላሽ
መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን
ኢየሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር
እንደ ኢየሱስ በምድር ላይ
ፈልጌ አጣሁ እርሱን መሳይ
ስለዚህ እኔ አመልካለሁ
ቀሪ ዘመኔ ኢየሱስ ነው



Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye



Attention! Feel free to leave feedback.