Bereket Tesfaye - Kal Alegn Lyrics

Lyrics Kal Alegn - Bereket Tesfaye




ፈውስን ፍልጌ ስንከራተት
መፍትሄ አጥቼ ስባትት
አንዴ ወደዛ አንዴ ወዲህ ስል
እሩጬ ሩጬ ልቤ እስኪዝል
ከዚህ ሁሉ ጣጣ የገላገለኝ
የዳዊት ዘር ነው ቃልን የሰጠኝ
በአንዲት ቃል ብቻ ተገላገልኩኝ
ተባረክ ብዬ አመሰገንኩኝ
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ
ከጨለማ ውስጥ እኔን የጠራኝ
አስደናቂውን ብርሃን ያሳየኝ
የተናኩትን ብሎ ጠርቶ
በወንጌል ዘይት ራሴን ቀብቶ
የሚያየኝ ሁሉ እስኪገረም
አቆመኝ ጌታ ለምስክር
እንደ መልካሙ እንደዛ መሬት
ቃሉን ዘራብኝ አረኩኝ ሀሴት
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ
እንደ አብርሃም በድንቅ የጠራኝ
ሁሉንም ተወው ውጣ አትፍራ ያለኝ
እስከ ዓለም ፍጻሜ ከእኔ ጋራ ነው
የቃሉ መንፈስ በውስጤ ያለው
ስለዚህ አልፈራም አልሸበር
ድምፅን ሰማሁኝ ከእግዚአብሔር
ወድቄ የምቀር መቼ ሆንኩና
ጌታ ነግሮኛል ሄዳለሁ ገና
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
ቃል አለኝ በፍፁም አልወድቅም
ቃል አለኝ ጌታ የሰጠኝ
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ ቃል አለኝ
(ቃል አለኝ) በልጅነቴ (ቃል አለኝ) ቃል ገብቶልኛል
(ቃል አለኝ) እንደማይተወኝ (ቃል አለኝ) ጌታ ነግሮኛል
(ቃል አለኝ) ከአሁን በኋላ (ቃል አለኝ) የምኖረው
(ቃል አለኝ) ቃሉን ከፊቴ (ቃል አለኝ) አስቀድሜ ነው
ቃል አለኝ ቃል አለኝ



Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye



Attention! Feel free to leave feedback.