Gossaye Tesfaye - Tuxedo Lyrics

Lyrics Tuxedo - Gossaye Tesfaye



አላይ ቢል አይኗ መች አላየችኝ
በበራው ልቧ አይታ የፈቀደችኝ
ሊያውም እሷው ናት የህይወት መንገዴ
ተርፋ ከራሷ እኔን የመራችኝ
ታዲያ እሷን ለኔ ልቧ እሺ ቢላት
ከእጄ እንድትገባ በፍቅር አስገድዶ
ደምቆ ማጌጡን በእሷ አንዴ ለምዶ
ግድ የለኝ ዛሬ ባለብስም ቶክሲዶ
ወዳጄ አክብሮኝ የጠራኝ ግብዣ
ቀኑ እስኪቃረብ ጠፍቶኝ መድረሻ
እንዳይደርስ የለም ሰአቱም ደርሶ
ወጣሁ ለብሼ ውዱን ቶክሲዶ
ከግብዣው ቦታ ተጠርታ እንደኔ
የመጣች ቆንጆ አይቶ ያኔ አይኔ
ባጣ መልስ ካይኗ ውስጤ አንዴ ነዶ
በኔ አያምርም ወይ አልኩኝ እኔ ይህ ቶክሲዶ
አላይ ቢል አይኗ መች አላየችኝ
በበራው ልቧ አይታ የፈቀደችኝ
ያውም እሷው ናት የህይወት መንገዴ
ተርፋ ከራሷ እኔኑ የመራችኝ
ታዲያ እሷን ለኔ ልቧ እሺ ቢላት
ከእጄ እንድትገባ በፍቅር አስገድዶ
ደምቆ ማጌጡን በሷ አንዴ ለምዶ
ግድ የለኝ ዛሬ ባለብስም ቶክሲዶ
እንዲህ አይነት ግብዣ አላውቅ አይቼ
ከመድረኩ ላይ አልኩኝ ወጥቼ
የኔ አነጋገር እንደ እድል ሆኖ
ልቧ አስተዋለኝ ያን ግዜ አይኗ ጨፍኖ
አውቂያት አውቃኝ ቀርባኝ ላመታት
ይኸው እስከዛሬ ሆነችኝ ብርታት
አይቶላት ውስጤ ልቤ እሷን ፈቅዶ
ኖራለች በቃ ትርፍ ነህ ላይኗ ቶክሲዶ



Writer(s): Gosaye Tesfaye


Gossaye Tesfaye - Satamagne Bela
Album Satamagne Bela
date of release
01-12-2010




Attention! Feel free to leave feedback.