Rophnan - Yesew Qine Lyrics

Lyrics Yesew Qine - Rophnan



ብዬሽ ዓለሜ እያለሽ ከእኔ
ለካስ ሁለት ፊት ነሽ የሰዉ ቅኔ
የማየው የዋህ እርግብ መልክሽን
ፍቅር ጋርዶብኝ መብረርሽን
አዬ-ዬ ብላቴናው ኖረ ሲታገስ
አዬ-ዬ ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ
አዬ-ዬ ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ
አዬ-ዬ የፈታሁሽ የሰው ቅኔ
(ተው ምነው ክራሬ ተው ምነው)
(ከድታ የሄደችን ታመጣለህ ምነው)
ጀምረን ነበረ ፍቅርን እንድ ድውር
የጥጥ ቃላት ክምር
በቀናቶች ዝውር
ጥለቱን በመልኳ አሳምሬ ነድፌው
"ቋጪው" ብላት "እንቢ" ብቻዬን ጠልፌው
ዓባይን ብከተል ሰጠኝ ለፈርዖን
መጨረሻው ሀዘን ያንቺ አፍቃሪ መሆን
እራሴን ከልቤ አጣልተሽብኝ
ሰው አልሆንም ነበር እርሱ ባያየኝ
አዬ-ዬ ብላቴናው ኖረ ሲታገስ
አዬ-ዬ ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ
አዬ-ዬ ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ
አዬ-ዬ ፈታሁሽ የሰው ቅኔ
ጀምረን ነበረ ፍቅርን ማሾር እንደድውር
ፈትለን ነበር ቀጭን ፍቅር በቃላቶች ዝውር
ጥለቱን ልክ እንደመልኳ አሳምሬ ነድፌው
"ቋጪው ብላት "እንቢ" ብቻዬን ጠልፌው
አይ ብታዩ ማማሩን ድንቁን ስራዬን?!
ከኔ የዘረፈሽ መቼም የማይሰጥሽን
ብቻዬን ጠልፌ ላንቺ የሰራውትን ሸማ
ላደላት አስቀመጥኩላት ካልቋጨሽውማ
ግዕዝ ካልዕ ብሎ ሳልስን አስከትሎ
አስከትሎን አስከትሎ የጀመረው በአቦጊዳ
ለፍቅር ነበር እንግዳ፤ አይ እንግዳን አይ እንግዳ
ብላቴናው ኖሮ ሲታገስ
ቅኔ እስኪገባው ድረስ፤ ድረስ ድረስ
ወርቁን ያገኝሁለት ያኔ
ፈታሁሻ የሰው ቅኔ
(የሰው ቅኔ፣ የሰው ቅኔ፣ የሰው ቅኔ)
(ህ-ህ-ምም)
ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ
ይህወት እንደገና
ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ
እያየሁሽ ወደ ኋላ
ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ
ይህወት እንደገና
ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ
ግን ፊት የለም ግድ ነውና
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ምም)
(ህ-ህ-ም-ምምም ህ-ም-ም-ምምም)
(ዬ-ህ)



Writer(s): Rophnan


Rophnan - Reflection
Album Reflection
date of release
17-05-2018




Attention! Feel free to leave feedback.