Yosef Kassa - Leze New Lyrics

Lyrics Leze New - Yosef Kassa



ያን ያረክልኝ የማልረሳው
ለእኔ ብለህ ነው ሞቴን የሞትከው
ለሕይወቴ ቤዛ ባትሆን ኖሮ
የት እገኝ ነበረ ያኔ ድሮ (አዬ ያኔ ድሮ)
ሁሌ ይህን ሳስብ የሚደንቀኝ
በመስቀል ላይ ለእኔ ያዋልክልኝ
ያኔ በሰራኸው ታላቅ ስራ
ሕይወትን አገኘሁ እንደገና (አዬ እንደገና)
አዝ ለዚህ ነው ሁሌ ምዘምረው
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ገና ከዚህም በላይ አመልካለሁ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
እኔስ ደስ አለኝ የአንተ በመሆኔ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ከምንም በላይ ልዩ ነህ ለእኔ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ከአንተ ጋራ ሆኖ ማነው የከሰረ
አንተን ተጠግቶ ኧረ ማን አፈረ
ለቀረቡት ሁሉ መልካም የሚያደርግ
እስቲ እንደኢየሱስ ኧረ ማነው ደግ (፪x)
እናት እንኳን ልጇን ብትረሳው
የነበራት መውደዷ ቢረሳት
አንተ አትለወጥ እንደሰዉ
የአንተ የዘለዓለም ፍቅር ነዉ (አዬ ፍቅር ነው)
ሁልጊዜ አንተ ከእኔ ጋራ
ታበረታኛለህ እንዳልፈራ
ከእናት አባት በላይ የሆንከኝ
በአንተ ተደግፌ አረፍኩኝ (አዬ አረፍኩኝ)
አዝ ለዚህ ነው ሁሌ ምዘምረው
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ገና ከዚህም በላይ አመልካለሁ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
እኔስ ደስ አለኝ የአንተ በመሆኔ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ከምንም በላይ ልዩ ነህ ለእኔ
ሁሌ ከእኔ ጋር ያለ እንደ አንተ ሰለሌለ
ከአንተ ጋራ ሆኖ ማነው የከሰረ
አንተን ተጠግቶ ኧረ ማን አፈረ
ለቀረቡት ሁሉ መልካም የሚያደርግ
እስቲ እንደኢየሱስ ኧረ ማነው ደግ (፪x)
ልክ እንደ ጌታዬ ኧረ ማነው ደግ
ሕይወቱን የሰጠኝ ኧረ ማነው ደግ
ወድሃለሁ ብሎ ኧረ ማነው ደግ
ልጁ ያደረገኝ ኧረ ማነው ደግ (፫x)



Writer(s): Samuel Alemu, Yosef Kassa


Yosef Kassa - Kidan Alegn
Album Kidan Alegn
date of release
12-06-2019




Attention! Feel free to leave feedback.