Gigi - Body paroles de chanson

paroles de chanson Body - Gigi



ተው ሽሸኝ አልሸሽም
ተው ሸሸኝ አልሸሽም
እንዲያ ስንባባል አለብኝ
ጭልምልም ጭልምልም
ተው ሽሸኝ አልሸሽም
ተው ሸሸኝ አልሸሽም
እንዲያ ስንባባል አለብኝ
ጭልምልም ጭልምልም ጭልምልም
አንተ አገርህ ወዲያ
አንተ አገርህ ወዲያ ከወንዙ ባሻገር
የኔ አገር ከወዲህ ወንዙን ሳንሻገር
ታዲያ ምን አለበት
ያም አገር ይሄም አገር
እስኪ ስሞትልህ ስቀበር አንተ ልጅ
የዛሬን ከኔ እደር
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ግርማው እንደ ታቦት ከሩቅ የሚያስፊራ
ምነው ሳየው ውዬ ሲነጋ ባየው
እሱ አምላክ አይደለም እኔ አልሰግድለትም
ብቻ እግሩን ልሳመው አይሂድብኝ የትም
ዝንጥፍ ዝንጥፍ ያለ የበቆሎ ዛላ
ሰውነቱ እሽት ነው ተጠብሶ ሚበላ
እሽት እሽት ነው ሳይወጣ ከእፍኝ
ቃም ቃም አረኩት እኔስ ምኔ ሞኝ
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ተው ሽሸኝ አልሸሽም
ተው ሸሸኝ አልሸሽም
እንዲያ ስንባባል አለብኝ
ጭልምልም ጭልምልም
ተው ሽሸኝ አልሸሽም
ተው ሸሸኝ አልሸሽም
እንዲያ ስንባባል አለብኝ
ጭልምልም ጭልምልም ጭልምልም
አንተ አገርህ ወዲያ
አንተ አገርህ ወዲያ ከወንዙ ባሻገር
የኔ አገር ከወዲህ ወንዙን ሳንሻገር
ታዲያ ምን አለበት
ያም አገር ይሄም አገር
እስኪ ስሞትልህ ስቀበር አንተ ልጅ
የዛሬን ከኔ እደር
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ወጋ ወጋ አረገኝ አንጀቴን ልቤን
ምነው ታመኛለህ ስጠኝ ጤናውን
ከአፍህ ከሚፊሰው ከማር ከወለላ
ይሻለዋል ቀምሶ ይሄ የፍቅር ገላ
ገላ ሰውነቱ እንደእናቴ ጡት
ያኔ በልጅነት እንደጠባሁት
ወተት ወተት አለ የኔም ሰውነቴ
አይን አይኑን እያየሁ ወይ መንከራተቴ
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ
ሀገሩን አላውቀው መንደሩን
መጣው ፍለጋ ሸጋውን
ገላ ገላ ገላ ገላ ገላ
እርቦኝ አንተን ካላየሁ አልበላ...



Writer(s): Chris Ballew, David Michael Dederer, Jason S. Finn


Gigi - One Ethiopia
Album One Ethiopia
date de sortie
01-01-1998




Attention! N'hésitez pas à laisser des commentaires.